በዲሞክራቲክ ኮንጎ የኢቦላ ቫይረስ ወረርሽኝ በድጋሚ ተቀሰቀ፡፡

የሀገሪቱ ባስልጣናት እንዳስታወቁት የኢቦላ ቫይረስ ወረርሽኝ በምዕራባዊቷ የ ኮንጎ አምባንዲካ ከተማ በድጋሚ ተከስቷል፡፡

ወደ ሀገሪቱ መዲና ኪንሻሳ መደበኛ የመጓጓዣ አገናኝ ያላት እና የ 1 ነጥብ 5 ሚሊዮን ህዝብ የንግድ ማዕከል በሆነችው አምባዲካ ከተማ 6 ሰዎች ላይ ቫይረሱ ተገኝቷል፡፡

ከነዚያ መካከልም 4ቱ በቫይረሱ ምክንያት ህይወታቸው አልፏል ነው የተባለው፡፡

ከተማዋ የኢቦላ ቫይረስ ወረርሽኝ በተከሰተባት እና ከ 2ሺ 200 በላይ ሰዎች በቫይረሱ ምክንያት በሞቱባት የሀገሪቱ ሰሜናዊ ክፍል 1ሺ ኪሎ ሜትር ያህል ርቀት ላይ ትገኛለች፡፡

የሀገሪቱ ጤና ሚኒስትር በድጋሚ ወረርሽኙ ተቀስቅሷል፤ በፍጥነት ክትባት እና መድሀኒቶችን ወደ ከተማዋ እንልካለን ሲሉም ተሰምቷል፡፡

የኢቦላ ቫይረስ ከፍተኛ ትኩሳትን ፣ ማስመለስ እና ተቅማጥን የሚያስከትል ሲሆን በበሽታው ከተጠቁ ሰዎች በሚወጡ ፈሳሾች ንክኪ አመካኝነትም ከሰው ወደ ሰው ይተላለፋል ፡፡

በዴሞክራቲክ ኮንጎ ከአውሮፓውያኑ 2017 ወዲህ የኢቦላ ቫይረስ ወረርሽኝ 3 ጊዜ ተቀስቅሷል፡፡

ሀገሪቱ ከ6ሺ በላይ ሰዎችን በሞት ካጣችበት የኩፍኝ ወረርሽኝ እና አሁን ደግሞ ከ3ሺ በላይ ዜጎቿ በኮቪድ 19 ወረርሽኝ መያዛቸው እና 71ዱ ህይወታቸው ማለፉ ጋር ተደማሮ ችግሩን የከፋ አድርጎባታልም ነው የተባለው፡፡

የዓለም ጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ቴድሮስ አድሀኖም የኮሮና ቫይረስ ብቸኛው የጤና ስጋት አለመሆኑን በኮንጎ በድጋሚ የተቀሰቀሰው የኢቦላ ቫይረስ ወረርሽኝ ማሳያ ነው ማለታቸውን ሮይተርስ ዘግቧል፡፡

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን፣ዜናዎችን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ። https://t.me/ethiofm107dot8

በትግስት ዘላለም
ግንቦት 25 ቀን 2012 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *