ነውጥ እና ዘረፋውን በሀይል እንደሚያስቆሙ ፕሬዝዳንት ትራምፕ ተናገሩ።

በጥቁር አሜሪካዊው ጆርድ ፈሎይድ በፖሊስ በጭካኔ መገደልን ተከትሎ በአሜሪካ የተከሰተውን የህዝብ አመፅ ለማረጋጋትና ፌደራል ባለስልጣናትን ይጠብቁ ዘንድ ከዋሽንግተን 1 ሺህ 200 የብሔራዊ ጋርድ አባላት በተጨማሪ በመቶዎች የሚቆጠሩ የብሔራዊ ጋርድ ወታደሮች ከተለያዩ አምስት ግዛቶች ተልከዋል፡፡

እነዚህ ወታደሮች ነጩን ቤተ መንግስት፣ በዋና ከተማው የሚገኙትን ቅርሶችና ንብረቶች የመጠበቅ ሀላፊነት የተሰጣቸው ሲሆን የዲሲ ፖሊስንም ያግዛሉ፡፡

የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ የህዝቡን ተቃውሞ፤ የሀገር ውስጥ ሽብር እንጂ ፈፅሞ ሰላማዊ ተቃውሞ አይደለም ብለዋል፡፡

ንፁህ ህይወት ማጥፋትና የንፁህ ሰው ደም ማፍሰስ ኢ ሰብአዊና በእግዚአብሔር ላይ የሚፈፀም ወንጀል ነው ሲሉ ተናግረዋል፡፡

መዳን እንጂ ጥላቻ መሆን የበትም፣ፍትህ እንጂ ረብሻ መሆን የለበትም፤ የኛ ተልዕኮ ይሄ ነው፤ መቶ በመቶ ይሳካልናል ፤ ሀገራችን ሀሌም ታሸንፋለች ብለዋል፡፡

የአማሪካውያን ምርጥ ቀኖች ገና የሚመጡ ናቸው የሚሉት ዶናልድ ትራምፕ ክፋትና አመፅ ከነገሱብን ግን ማናችንም ነፃ አንሆንም ሲሉ ተናግረዋል፡፡

በጆዎርጅ ፍሎይድ የጭካኔ አሟሟት ሁሉም አሜሪካውያን ውስጣቸው ተብጥብጧል፣ ታሟል ያሉት ፕሬዝዳንቱ በከንቱ እንዳልሞተ ግን ቃል እገባለሁ ሲሉ ተናግረዋል፡፡

የፍሎይድ ትውስታ በቁጡ የተቃውሞ ሰልፈኞች መረሳት የለበትም ብለዋል፡፡

ስርአትን ለማስጠበቅ የተሰየምኩ የህግ ፕሬዝዳንታችሁ ነኝ፣ የሰላማዊ ተቃውሞም ደጋፊ ነኝ ሲሉ ተናግረዋል፡፡

ከቅርብቀናት ወዲህ ግን ሀገራችን ፤ በስርአት አልበኞች፣ በዘራፊወች ፣ በነውጠኞች፣ በወንጀለኞች በአመፀኞች ተወጥራለች ብለዋል፡፡

አሜሪካውያንን እና ንብረታቸውን ለመጠበቅ አለ የተባለውን፣ የሲቪል ሆነ የጦር ሙሉ አቅማችንን ተጠቅመን ይሄንን ነውጥ ዘረፋና ጥቃት እናስቆማለን ሲሉ ተናግረዋል፡፡

የተቀሰቀሰውን አመፅ ለማብረድ ሀይል ለመጠቀም እገደዳለሁ ብለዋል፡፡

ለስድስት ሌሊቶች የዘለቀወን ዘረፋና አመፅ እናቆማለን ሲሉም ቃል ገብተዋል፤
የመጀመርያውና ከፍተኛው እንደ ፕሬዝዳንት ያለብኝ ግዴታ ታላቋን ሀገራችንን እና ህዝቧን ከየትኛውም አዳጋ መከላከል ነው ሲሉ ቁርጠኝነታቸውን ገልፀዋል፡፡

ትራምፕ መግለጫውን እየሠጡ ካሉበት በመቶዎች የሚቆጠር ሜትሮች ውስጥ ተቃውሞ ሰልፈኞች ከፖሊስ ጋር መጋጨታቸውን ቀጥለው ነበር ብለው ነበር ብሎ ቢቢሲ ሲዘግብ።

ሪዮተርስ ደግሞ ከነጩ ቤተ መንግስት አቅራቢያ ሰላማዊ ሰልፈኞችን ለመበተን ፖሊስ አስለቃሽ ጭስና የላስቲክ ጥይት ተጠቅሟል ሲል በድረ ገፁ አስነብቧል፡፡

ትራምፕ ይሄንኑ ጉዳይ የተመለከተውን መግለጫ እየሰጡ ባለበት ወቅት ፍትህ አሁኑኑ የሚሉ ሰልፈኞች በብሩክሊን ጎዳና ተቃውሟቸውን ሲያሰሙ ነበር፡፡

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን፣ዜናዎችን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ። https://t.me/ethiofm107dot8

በሔኖክ አስራት
ግንቦት 25 ቀን 2012 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *