“የሞውሪንሆ ንግግር አነቃቅቶኛል” የሊቨርፑሉ ተከላካይ አንድሪው ሮበርትሰን

ሮበርትሰን -የሞውሪንሆ ንግግር አነቃቅቶኛል የሊቨርፑሉ የመስመር ተከላካይ አንድሪው ሮበርትሰን የቶተንሃሙ አሰልጣኝ አበርትተውኛል ይላል። ከ18 ወራት በፊት ሊቨርፑል በወቅቱ ሞውሪንሆ ያሰለጥኑት የነበረውን ማንቸስተር ዩናይትድ አንፊልድ ላይ 3ለ1 አሸነፈ። ውጤቱ ራሳቸውን “ልዩው ሰው” ብለው የሚጠሩትን አሰልጣኝ ስራቸውን ያሳጣቸው ነበር። ከመሰናበታቸው በፊት ግን የስኮትላንዳዊውን እንቅስቃሴ አድንቀዋል።

ሞውሪንሆ ከጨዋታው በኋላ በሰጡት አስተያየት “ሊቨርፑል ከኳስ ጋርና ያለኳስ የሚጫወተው 200mph ነበር። ሮበርትሰንን ማየት ብቻውን አድክሞኛል። በየደቂቃው 100 ሜትር ያፈተልክ ነበር። አጃኢብ ነው” ነበር ያሉት። ስካይ ስፖርት የማን ንግግር ተነሳሽነቱን እንደጨመረለት ለሮበርትሰን ጥያቄ ሲያቀርብለት “ማንቸስተር ዩናይትድን በአንፊልድ ከገጠምን በኋላ ጆዜ ሞውሪንሆ የተናገሩት ” ብሏል። “የዚያን ለት ያሳየነው ብቃት አስገራሚ ነበር። አስታውሰዋለሁ። በጣም ጥሩዎች ነበርን። የጨዋታ ብልጫ ወስደንባቸው ነበር።

የተገበርነው ታክቲክ እንከን የለሽ ነበር። “ለእኔ በየትኛው ጨዋታ ላይ ቢሆን ብዙ መሮጤ የማይቀር ነው። “ነገር ግን እነዚህ ነገሮች ሁልጊዜ ማድረግ የምትችላቸው ናቸው ። ነገሩን የምመለከተው በዚህ መንገድ ነው። የኳስ ንክኪህ ፣ ክሮሶችህ፣ ፓስ እና ሌሎች ነገሮች ትክክል የማይሆኑባቸው ቀናት አሉ ። “መቆጣጠር የሚቻለው በእያንዳነዱ ጨዋታ ብቃትን 100 በመቶ አውጥቶ መጠቀም መቻልን ነው። እኔ ለማድረግ የምሞክረውም ይሀለንኑ ነው።

“ጨዋታው ከክዊንስ ፓርክ ጋር የሚደረግ ሆነ የሻምፒየንስ ሊግ ፍጻሜ ለእኔ ልዩነት የለውም። “እግር ኳስ መጫወት እወዳለሁ። የሚከፈለን ደግሞ እንድንጫወት ነው። “ማድረግ የምወድደው ያንን ነው። እስከ መጨረሻዋ ፊሽካ ድረስ መሮጥ እንደምችል አምናለሁ ። “ሞውሪንሆ ያንን ሲል ስሰማ ደግሞ በራስ መተማመኔ እጅግ ከፍ ብሏል። ።

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን፣ዜናዎችን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ።

https://t.me/ethiofm107dot8

በአቤል ጀቤሳ

ግንቦት 25 ቀን 2012 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *