የቬንዙዌላው ፕሬዝዳንት ወደ ቴህራን አቅንተው ከኢራን ጋር በርካታ ስምምነቶችን እንደሚፈራረሙ ገለፁ።

ኢራን በነደጅ ዕጥረት ውስጥ ላለችው ሀገር ድጋፍ ካደረገች በኋላ ማዱሮ ከኢራን ጋር በኢነርጂና በሌሎች መስኮች የትብብር ስምምነት እንደሚያደርጉ ገልፀዋል፡፡

ራሴ ሄጄ የኢራንን ህዝብ አመሰግናለሁ ብለዋል ማዱሮ በብሔራዊ የቴሌቪዥን ጣቢያ ብቅ ብለው፡፡

ይሁንና ማዱሮ መቼ ወደ ቴህራን እንደሚጓዙ ግን የገለፁት ነገር የለም፡፡

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን፣ዜናዎችን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ። https://t.me/ethiofm107dot8

በሔኖክ አስራት
ግንቦት 25 ቀን 2012 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *