የማዕከሉ ዋና ዳይሬክተር ዶክተር እስማኤል ሸምሰዲን እንዳሉት ባለፉት ሁለት ወራት ማዕከሉ 1 ሺህ 200 ታማሚዎችን መያዝ እንዲችል ተደርጎ ተደራጅቷል።
ማዕከሉ 40 የጽኑ ሕሙማን መኝታዎችና 1 ሺህ ጽኑ ያልሆኑ ሕሙማን ታካሚዎች አገልግሎት መስጠት ይችላል።
ጎን ለጎንም የላቦራቶሪ፣ የመድሃኒት ቤት፣ የጤና ባለሙያዎች ልብስ መቀየሪያ፣ መታጠቢያዎችና ሌሎች ክፍሎችም ተዘጋጅተዋል።
በማዕከሉ ተኝተው ለሚታከሙ ሕሙማንና ለጤና ባለሙያዎች አስፈላጊ ግብዓቶች መሟላታቸውንም ጠቅሰዋል።
በተጓዳኝም ከማዕከሉ የጥበቃ ሠራተኞች ጀምሮ የሕክምና አገልግሎት ለሚሰጡ ነርሶችና ዶክተሮች ሥልጠናም ተሰጥቷል።
በዚህ መሰረት የማዕከሉ ዝግጅት ተጠናቆ ዛሬ ሐሙማንን መቀበል መጀመሩን ነው ዶክተር እስማኤል ለኢዜአ ተናግረዋል።
በማዕከሉ ሕሙማን አስፈላጊውን አገልግሎት እንዲያገኙ፤ የጤና ባለሙያዎችና ሌሎች ሠራተኞችም ለቫይረሱ ተጋላጭ እንዳይሆኑ ትኩረት መሰጠቱንም አክለዋል።
በተለይም የአየር ሥርዓት ፍሰቱን ለማስተካከል የሚረዱ መሣሪያዎች መገጠማቸው ተጋላጭነትን ለመቀነስ አስተዋጽኦ እንዳላቸው አስረድተዋል።
ከማዕከሉ የሚወገዱ ፍሳሾች ለብቻ እንደሚወገዱና ደረቅ ቆሻሻዎችም በዘመናዊ መሣሪያ በመታገዝ የሚወገዱ መሆኑንም ዶክተር እስማኤል ተናግረዋል።
በማኅበረሰቡ ዘንድ የኮቪድ-19 ማዕከላትን የመፍራት ሁኔታዎች መኖሩን የጠቆሙት ዶክተር እስማኤል ይህ አመለካከት ሊቀየር እንደሚገባም አሳስበዋል።
በዚህ ረገድ በማዕከሉ ለሕሙማን የጤና ትምህርቶችና የአካል ብቃት እንቅስቃሴም ጭምር ለመሥጠት ዝግጅት መደረጉን ተናግረዋል።
ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን፣ዜናዎችን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ። https://t.me/ethiofm107dot8
ኢትዮ ኤፍ ኤም የኢትዮጵያዊያን
ግህንቦት 25 ቀን 2012 ዓ.ም











