የዘጠኝ አመት ኬንያዊ ታዳጊ ከእጅ ንክኪ የራቀ የእጅ መታጠቢያ በመስራት ተሸላሚ ሆነ፡፡

የኬኒያው ታዳጊ ለሽልማት የበቃው ከበርካታ የሀገሩ የፈጠራ ባለሙያዎች ጋር ተወዳድሮ ነው፡፡

የዘጠኝ አመቱ ታዳጊ ስቴፈን ዋሙኮታ የእጅ መታጠቢያውን የሰራው ከእንጨት ነው፤ቢቢሲ እንዳለው ይህ አዲሱ የታዳጊው ፈጠራ ውጤት ሰዎች ሲታጠቡ ከእጅ ንክኪ ውጪ በሆነ መልኮ እንዲታጠቡ የሚያደርግ ነው፡፡

ታዳጊው እንደሚለው ይህንን የፈጠራ ውጤት እንዲሰራ ያነሳሳው በሚኖርባት ምዕራብ ኬንያ ያለው ለኮሮና ቫይረስ በሚያጋልጥ ሁኔታ የእጅ ንክኪ የበዛበት መሆኑን ተናግሯል፡፡

ሲቴፋን ሲናገር ይህንን ሲሰራ ታዲያ በአናጢነት የሚተዳደረው አባቱ እንዳገዘው ለቢቢሲ ተናግሯል።

ይህ የዘጠኝ አመቱ ስቴፈን በኮሮና ወቅት የተለያዩ የፈጠራ ስራዎችን በመስራት ያበረከቱ 68 ሰዎች ጋር ነው ተሸላሚ የሆነው።

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን፣ዜናዎችን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ። https://t.me/ethiofm107dot8

በያይኔአበባ ሻምበል
ግንቦት 25 ቀን 2012 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *