81 በመቶ ማላዊያን ከኮሮና ቫይረስ ይልቅ ርሀብ እንደሚያሰጋቸው ተናገሩ።

የሀገሪቱ የህዝብ አስተያየትና ምርምር ተቋም ከስዊድን ተመራማሪዎች ጋር በመሆን በአውሮፓውያ ከግቦት 7 እስከ 28 ባለው ጊዜ ውስጥ ባካሄዱት ጥናት መሰረት 81 በመቶ የሚሆኑት የሀገሪቱ ዜጎች ስጋታቸው ወረርሽኙ ሳይሆን ርሀብ ነው ተብሏል፡፡

እድሜአቸው ከ55 ዓመት በላይ የሆኑ ሰዎች ደግሞ ከወጣቶች በይበልጥ የርሀብ ስጋታቸው ከፍ እንደሚል ተነግሯል፡፡

መረጃውን ከሰጡት 60 በመቶ ያህሉ ደግሞ የሀገሪቱ የጤና አጠባበቅ ስርዓት ላይ እምነረት የላቸውም፡፡

76 በመቶ ያህል ሰዎች ደግሞ በወረርሽኙ ከተያዙ በኋላ ስለሚኖረው ማህበረሰባዊ መገለል ከፍተኛ ስጋት ውስጥ ናቸው፡፡

በሀገሪቱ የሚገኙ የጤና ባለሙያዎች ከፍተኛው የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ በሀገሪቱ ሊቀሰቀስ እንደሚችል ምልክቶች እየታዩ መሆናቸውን በተደጋጋሚ በማሳሰብ ላይ ናቸው ሲል ቢቢሲ ዘግቧል፡፡

እስካሁንም በሀገሪቱ 336 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ ሲያዙ 4 ሰዎች ደግሞ በቫይረሱ ምክንያት ህይወታቸውን አጥተዋል፡፡

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን፣ዜናዎችን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ። https://t.me/ethiofm107dot8

በትግስት ዘላለም
ግንቦት 25 ቀን 2012 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *