መቀመጫውን እስራኤል ያደረገው ፒስ ሜድ ኩባንያ ለቅዱስ ፖውሎስ ሆስፒታል 50 የህጻናት ህክምና አልጋዎችና 18 ኢንፊውዥን ፖንፖችን ለግሷል፡፡

የሆስፒታሉ የኮሚኒኪሽን ሀላፊ አቶ ነዋይ ጸጋዬ ለኤትዮ ኤፍ ኤም እንዳሉት ይህ ኢንፊውዥን ፖንፕ በተለይ ለህጻናት ድንገተኛ ህክምና ክፍል ከፍተኛ አገልግሎት የሚሰጥ ነው፡፡

የተቋሞ የስራ ሀላፊዎች የዛሬ አመት በኮሌጁ ጉብኝት ባደረጉበት ወቅት የነበረብንን የህክምና ቁሳቁሶች ነግረናቸው ነበር በዛ መሰረትም የህክምናው የጀርባ አጥንት የሆኑ መሳሪያችን አበርክተውልናል ብለዋል አቶ ንዋይ።

የፒስ ሜድ ድርጅት ዋና ፕሬዝደንት አቶ ውበቱ ወርቁ ለኮሌጁ ዋና ሀላፊ ዶ/ር ወንድማገኝ ገዛኸኝ እርዳታውን በዛሬው እለት አስረክበዋል፡፡

ዶ/ር ወንድማገኝ በርክክቡ ወቅትም ድርጅቱ ይህንን ድጋፍ በማድረጉ አመስግነዋል፡፡
በተለይ ድጋፉ ኢትዮጲያ የእናቶችንና የህጻናትን ሞትን ለመቀነስ ለምታደርገው ትግል ቁልፍ ሚና አለው ብለዋል፡፡

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን፣ዜናዎችን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ። https://t.me/ethiofm107dot8

በያይኔ አበባ ሻምበል
ግንቦት 26 ቀን 2012 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.