በዓለማችን ከ450 ሺህ በላይ የሕክምና ባለሙያዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸውን አቀፉ የነርሶች ካውንስል አስታወቀ።

ከተጠቂ የህክምና ባለሙያዎች መካከል 600 ነርሶች በዚሁ ቫይረስ ምክንያት ህይወታቸውን እንዳጡ ተገልጿል።

በዓለማችን በኮሮና ቫይረስ ከተጠቁ ከ6.4 ሚሊየን በላይ ዜጎች ውስጥ 450 ሺህ የሚሆኑት የህክምና ባለሙያዎች ናቸው ተብሏል።

ከ600 በላይ የሚሆኑ ነርሶች በአለም ዙሪያ በኮቪድ-19 መመቶታቸው ሲነገር ከ450 ሺህ በላይ የህክምና ባለሙያዎች ደግሞ በቫይረሱ መያዛቸው ይገመታል ብሏ አለም አቀፉ የነርሱች ካውንስል፡፡

ባለፉት ሁለት ወራት በዓለም ዙሪያ ባለው የኮሮና ቫይረስ ወረሽኝ ምክንያት የነርሶች ሞት ቁጥር ከ100 ወደ 600 ከፍ ማለቱንም ካውንስሉ ገልጿል።

በዓለም ዙሪያ በቫይረሱ ሊጠቁ የሚችሉ የጤና ባለሙያዎች ብዛት ደግሞ 450 ሺህ እንደሚገመት በጄኔቫ መሰረቱን ያደረገው አለም አቀፉ የነርሱች ካውንስል ዋና ስራ አስፈጻሚ ሃዋርድ ካተን ለሮይተርስ ተናግረዋል፡፡

እነዚህ ቁጥሮች እየጨመሩ የሚሄዱ ናቸው” ሲሉም ስራ አስፈጻሚው ተናግረዋል፡፡

ወረሽኙ የጤና ባለሙያዎች እየከፈሉት ያለውን እውነተኛ ዋጋ እያሳየ ነው እና ለእነሱ ከፍተኛ ጥበቃና አስተማማኝ መረጃ እንዲሰጥ ጥሪያቸውን እንዳቀረቡ ዘገባው ጠቁሟል።

በአማካይ 7 በመቶ የሚሆኑትን በኮቪድ-19 ምክንያት የሚከሰተው የሳንባ በሽታን በማከሙ ረገድ የእነርሱ ድርሻ ነው ፣ ይህ ማለት ነርሶች እና ሌሎች ሰራተኞች ከፍተኛ የግል ተጋላጭነታቸው ይጨምራል፡፡

ምክንያቱም እነሱ የሚንከባከቧቸው ህመምተኞች ናቸው እና ይላሉ ዋና ስራ አስፈጻሚው

ሮይተርስ እንደሚለው በአለም ዙሪያ ከተመዘገበው ከ6.4 ሚሊየን በላይ የኮሮና ቫይረስ ተጠቂዎች ውስጥ 450 ሺህ የሚሆኑን የህክምና ባለሙያዎች መሆናቸው ተገልጿል።

በህክምና ባለሙያዎች መካከል የሚከሰተው የተጠቂዎች ቁጥር እንደሀገሮቹ የሚለያይ ሲሆን ለምሳሌም በሲንጋፖር ከኮሮና አጠቃላይ ተጠቂዎች ውስጥ 1 በመቶዎቹ የጤና ባለሙያዎች ሲሆኑ በአየርላንድ ደግሞ ከ30 በመቶ በላይ ናቸው፡፡

ስፔን እና ጀርመን በኮቪድ-19 የተያዙት ሰዎች ቁጥር ከፍተኛ ቢሆንም በጤና ባለሙያዎች ላይ የደረሰው ሞት ግን አነስተኛ ነው ተብሏል፡፡

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን፣ዜናዎችን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ። https://t.me/ethiofm107dot8

በያይኔአበባ ሻምበል
ግንቦት 26 ቀን 2012 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *