በፌደራል ማረሚያ ቤቶች ኮሚሽን ስር ያሉ የህግ ታራሚዎች ከ60 ሺህ ባላይ የአፍ እና የአፍንጫ ጭንበል ማምረታቸው ተገለጸ፡፡

የፌደራል ማረሚያ ቤት ባስገነባው የጋርመነት ኢንዱስትሪ ውስጥ የህግ ታራሚዎች 60 ሺህ 300 ያህል ጭምብል እንዳመረቱ ነው የተገለጸው፡፡

የፌደራል ማረሚያ ቤቶች ያስገነባው ከፍተኛ ጥበቃ ማረሚያ ቤት የጋርመነት ኢንዱስትሪ ሥራ መጀመሩንም ተገልጻል፡፡

ኢንዱስትሪው የኮሮና ቫይረስን ለመከላከል የሚያስችል የአፍና የአፍንጫ መሸፈኛ ጭንብል ማምረት መጀመሩን በፌደራል ማረሚያ ቤት ኮሚሽን የህዝብ ግንኙነት ሀላፊ አቶ ገረመው በላይ ለኤትዩ ኤፍ ኤም ተናግረዋል።

ጭንበል የማምረት ሥራ እንደተጠናቀቀ የራሳቸው አልባሳት ማምረት እንደሚጀምሩም ሃላፊው ገልጸዋል፡፡

በሔኖክ ወ/ገብርኤል
ግንቦት 26 ቀን 2012 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.