የሊቢያ ተፋላሚ ወገኖች 3ኛውን ድርድር ለማካሄድ ተስማሙ።

ዓለም አቀፍ እውቅና ያለው የሊቢያ መንግስት እና ኮማንደር ካሊፋ ሀፍታር ሊቢያን በሁለት ቦታ ከፍለው መታኮስ ከጀመሩ ዓመታት አስቆጥረዋል።

የነዳጅ ድፍድፍ ሀብታሟ አገር ሊቢያ ምድር እሚዋጉት ሁለቱ ተፋላሚዎች ይሁኑ እንጂ ከጀርባቸው ብዙ አገራት አሉ።

አልጀዚራ እንደዘገበው ከሆነ ግን በኮሮና እና በእስልምና የጾም ወቅትም ቢሆን ጦርነት ያላቆሙት እነዚህ ተፋላሚ ወገኖች አሁን ላይ ከሶስት ወራት በፊት ያቋረጡትን ድርድር እንደ አዲስ ለመጀመር ተስማምተዋል።

በሊቢያ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ተልዕኮ እንዳስወቀዉ ዓለም አቀፍ ዕዉቅና ያለዉ የሊቢያ መንግሥትና ኮማንደር ኸሊፋ ሐፍጣር የሚመሩት ቡድን በተኩስ አቁም እና በሌሎች ጉዳዮች ዙሪያ ለመወያየት እንፈልጋለን ብለዋል።

ከነዚህ የሊቢያ ተፋላሚ ሀይሎች ጀርባ ብዙ አገራት ያሉ ሲሆን ዓለም አቀፍ ዕዉቅና ያለዉን መንግስት ቱርክ ፈረንሳይ አሜሪካ እና ሌሎች የአውሮፓ አገራት ሲደግፉ ኸሊፋ ሐፍጣርን ደግሞ ሩሲያ የተባበሩት አረብ ኢምሬት ሳውዲ አረቢያ ግብጽ እና ሌሎች አገራት ድጋፍ ያደርጋሉ።

እንዚህ አገራት ሁለቱን ተፋላሚዎች እያዋጉ የሊቢያን ነዳጅ ወደ አገራቸው ያጓጉዛሉ።

ሁለቱ ተፋላሚዎች ባሳለፍነዉ የካቲት ለመጨረሻ ጊዜ ባደረጉት ድርድርም ተኩስ ለማቆም ተስማምተዉ የነበረ ቢሆንም ስምምነቱን በቀናት ውስጥ ጥሰውታል።

በጦርነቱ ሽንፈት እየደረሰበት ያለው ካሊፋ ሐፍጣር ጦር ትሪፖሊን ለመያዝ ካለፈዉ ዓመት ጀምሮ በተደጋጋሚ የከፈተዉ ጥቃት በመክሸፉ ያሁኑ ድርድር ምናልባት ዉጤት ያመጣል የሚል ተስፋ አሳድሯል።

ይሁንና እነዚህ ተፋላሚ ወገኖች ድርድሩ መቼ እና የት እንደሚያካሂዱ እስካሁን አልታወቀም።

ከ9 ዓመት በፊት የመሀመድ ጋዳፊ አምባገነናዊ ስርዓት አንግሸገሸን ዲሞክራሲ እንፈልጋለን በሚል ወደ አደባባይ የወጡት ሊቢያውያን አሁን ላይ በሰላም ወጥተው መግባት ናፍቋቸዋል።

ሊቢያውያን እንደቀልድ የጀመሩት አመጽ የጋዳፊን አገዛዝ ለመገርሰስ ቢጠቅማቸውም የአገራቸው እጣ ግን የጎበዝ አለቆች የጦር አውድማ ከመሆኗ ባለፈ የሊቢያን ድፍድፍ ነዳጅ መመንተፍ የፈለጉ የዓለማችን አገራት ሽኩቻ ላይ ናቸው።

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን፣ዜናዎችን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ። https://t.me/ethiofm107dot8

በሳሙኤል አባተ
ግንቦት 26 ቀን 2012 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *