127 ጋዜጠኞች በኮሮና ቫይረስ ምክንያት መሞታቸውን ዓለም አቀፉ የጋዜጠኞች ጥበቃ ቡድን አስታወቀ።

ባለፉት ሶስት ወራት ውስጥ በ31 የአለማችን ሀገራት የሚገኙ 127 ጋዜጠኞች በኮቪድ -19 ህይወታውን ማጣታቸውን በጂኒቫ መሰረቱን ያረገው የጋዜጠኞች መብት ጥበቃ ቡድን አስታውቋል፡፡

የተቋሙ ዋና ጸሐፊ ብሌይስ ሎፖን በሰጡት መግለጫ “የሚዲያ ሠራተኞች የኮሮና ቫይረስ ወረሽኝን ለመዋጋት በሚደረገው ውጊያ ላይ ትልቅ ሚና ይጫወታሉ ብለዋል፡፡

ከእነዚህ መካከል ብዙዎቹ ሥራቸውን በሚያከናውንበት ጊዜ በቂ የመከላከያ መሳሪያዎችን ባለመገኘታቸው ሕይወታቸውን አጥተዋል ሲሉ ያክላሉ፡፡

መንግስታዊ ያልሆነው ድርጅት ባደረገው ቆጠራ መሠረት እ.ኤ.አ. በሚያዚያ 1 እና በግንቦት 31 መካከል ቢያንስ 127 ጋዜጠኞች በ COVID-19 ምክንያት ሞተዋል ፡፡

ከእነሱ መካከል ሁለት ሦስተኛ የሚሆኑት በሥራ ላይ የነበሩ ሲሆን በግንቦት ወር ብቻ 72 ጋዜጠኞች በኮሮና ቫይረስ ተይዘዋል ፡፡

ከነዚህ ውስጥ ከፍተኛ ቁጥር የተመዘገበው በላቲን አሜሪካ ሀገራት ሲሆን ቢያንስ 62 ጋዜጠኞችን በኮሮና ቫረስ ተይዘዋል።

ሌላኛው ከፍተኛ የጋዜጠኞች ተጠቂ አህጉር ደግሞ አውሮፓ ሲሆን በዚያም 23 ጋዜጠኞች በቫይረሱ ህይወታቸውን አተዋል፡፡ በእስያ 17 ፣ ሰሜን አሜሪካ 13 እና አፍሪካ 12 ጋዜጠኞች ሞተዋል ፡፡

ፔሩ ከፍተኛ የተጠቂዎች ቁጥር ያላት ሀገር ናት 15 ፣ ቀጥሎም ብራዚል እና ሜክሲኮ እያንዳንዳቸው 13 ተጠቂዎች ያሏቸው ሲሆን በኢኳዶር ደግሞ 12 ናቸው፡፡

በአሜሪካ ውስጥ 12 ተጠቂዎች እንዲሁም በሩሲያ እና ፓኪስታን እያንዳንዳቸው 8 ጋዜጠኞች በኮሮና ቫይረስ ሳቢያ ህይወታቸውን አተዋል፡፡

ቀጥሎም በእንግሊዝ አምስት ፤ በባንግላዴሽ አራት ሞት ተመዝግቧል ፣ በቦሊቪያ ሶስት ፣ ካሜሩን ፣ ዶሚኒካን ሪፐብሊክ ፣ በፈረንሣይ ፣ በሕንድ ፣ በጣሊያን እና በስፔን ይገኙበታል ፡፡

በአልጄሪያ ፣ በኮሎምቢያ ፣ በግብፅ ፣ በስዊድን ሁለት ሁለት ተጠቂዎች ተለይተው ታውቀዋል፡፡

እንዲሁም አንድ አንድ ተጠቂዎች ያስመዘገቡ ሀገራት ኦስትሪያ ፣ ቤልጂየም ፣ ካናዳ ፣ ኢራን ፣ ጃፓን ፣ ሞሮኮ ፣ ኒኳራጓ ፣ ናይጄሪያ ፣ ደቡብ አፍሪካ ፣ ቶጎ እና ዚምባብዌ ናቸው ፡፡

ከዚህም በተጨማሪ ሌሎች የሚዲያ ሰራተኞች በቫይረሱ መያዘቸው ሲራጋገጥ አንዳንድ ሚዲያዎች ለጊዜው መዘጋት ነበረባቸው ማለቱን አናዶሉ ዘግቧል፡፡

ይህ ተቋም ቆጠራውን ያካሄደው በዓለም ዙሪያ የጋዜጠኞች ፣ የአካባቢ ሚዲያዎች እና ዘጋቢዎችን ብሔራዊ ማህበራት ጨምሮ በብዙ ምንጮች ላይ ተመስርቱ መሆኑን አስታውቋል።

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን፣ዜናዎችን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ። https://t.me/ethiofm107dot8

በያይኔአበባ ሻምበል
ግንቦት 26 ቀን 2012 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *