በሃንጋሪ ደጋፊዎች የማህበራዊ ርቀትን መመሪያ መጣሳቸው ተነገረ::

በሃንጋሪ ደጋፉዎች የማህበራዊ ርቀትን መመሪያ መጣሳቸው ተነገረ ትላንት የሃንጋሪ የጥሎ ማለፍ ዋንጫ ፍጻሜ ሲከናወን የተወሰኑ ደጋፊዎች የማህበራዊ ርቀት ደንብን መጣሳቸው ተነገሯል ።

67ሺ 215 ሰው የመያዘቅ አቅም ባለው ፑሽካሽ አሬና የታችኛው ክፍል ላይ ብቻ ደጋፊዎች ተራርቀው በመቀመጥ እንዲመለከቱ ተፈቅዶላቸው ነበር። ጨዋታውን ቡዳፔሽት ሆንቬድ 2ለ1 በሆነ ውጤት ሜዞኮቬስ ዦሪን አሸንፏል። አብዛኞቹ ደጋፊዎች መመሪያውን አክብረዋል።

ከእነዚህ በተቃራኒ ግን በሁለቱ ጎሎች ጀርባ በርከት ያሉ ሰዎች እጅብ ብለው ታይተዋል። ይህም ወደ ፊት ተመልካቾችን እንዴት ባለ መልኩ ማስተናገድ እንደሚኖርባቸው ለሃገሪቱ የእግር ኳስ ባለስልጣናት ጥሩ መልዕክት አስተላልፏል።

ሃንጋሪ ከኮቪድ 19 ወረርሽኝ በኋላ ተመልካቾች ወደ ስታዲየም እንዲገቡ የፈቀደች የመጀመሪያዋ ሃገር ሆናለች።

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን፣ዜናዎችን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ።

https://t.me/ethiofm107dot8

በአቤል ጀቤሳ

ግንቦት 27 ቀን 2012 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *