በጉራጌ ዞን የኮሮና ቫይረስ ተጠቂ ከሆነች ግለሰብ ጋር ንክኪ የነበራቸው 47 ሰዎች ወደ ለይቶ ማቆያ መግባታቸው ተገለጸ፡፡

በጉራጌ ዞን ቸሃ ወረዳ እናትየ ቀበሌ ነዋሪ የሆነች የ28 አመት እድሜ ያላት ሴት አዲስ አበባ ለቅሶ ደርሳ የተመለሰች እንስት በኮሮና ቫይረስ መያዟ በመረጋገጡ ወደ ለይቶ ማከሚያ መግባቷ ተገልጿል።

ቫይረሱ ያለበት ይህች እንስት አሁን ላይ በጥሩ ጤንነት ላይ እንደምትገኝም የጉራጌ ዞን ጤና ቢሮ አስታውቋል፡፡

የወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ ሪፈራል እና ቲቺንግ ሆስፒታል ሃላፊ ዶ/ር አብዱርሰመድ ወርቁ ከግለሰቧ ጋር ቀጥተኛ ግንኙነት የነበራቸው 13 ሰዎች ወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ ለይቶ ማቆያ መግባታቸውንም ተናግረዋል፡፡

በተመሳሳይ ቸሃ ወረዳ ላይ አዲስ አበባ ለቅሶ ደርሰው የተመለሱና ከእነኝህ ጋር ንክኪ የነበራቸው የተባሉ 34 ሰዎች ወደ ማቆያ መግባታቸውንም የዞኑ ጤና ቢሮ ጨምሮ ገልጿል፡፡

ከዚህ በፊት በተጓዳኝ በሽታ ቡታጅራ አጠቃይ ሆስፒታል ለሌላ በሽታ ህክምና እያደረገ የነበረ ወንድ ቫይረሱ ተገኝቶበት ሙሉ ለሙሉ አገግሟል፡፡

እስካሁን ድረስ በጉራጌ ዞን ሁለት የኮሮና ቫይረስ ተጠቂዎች እንዳሉም ነው ዞኑ ያስታወቀው፡፡

በዞኑ ውስጥ በ68 ቦታዎች ወልቂጤ ዩኒቨርሲቲን ጨምሮ 1ሺህ 280 ንክኪ ያላቸውን ሰዎች መያዝ የሚችሉ የለይቶ ማቆያዎች ማዘጋጀቱን የዞኑ ጤና ቢሮ ገልጿል፡፡

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን፣ዜናዎችን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ። https://t.me/ethiofm107dot8

በሔኖክ ወ/ገብርኤል
ግንቦት 27 ቀን 2012 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *