ብራዚል ባለፉት 24 ሰዓት በኮሮና ቫይረስ ምክንያት ከፍተኛ ሞት የተመዘገበባት የዓለማችን አገር ሆናለች።

የሀገሪቱ ጤና ሚኒስትር በሀገሪቱ በኮሮና ቫይረስ ምክንያት የተከሰተውን ከፍተኛ ሞትና የተጠቂዎች ቁጥር ይፋ አድርጓል፡፡

በሀገሪቱ አዲስ ከፍተኛ ሟቹች ቁጥር ተብሉ የተመዘገበው 1 ሺህ 349 ነው

እንዲሁም በአንድ ቀን ብቻ 28 ሺኅ 633 ሰዎች በቫይረሱ ተይዘዋል፡፡

በዚህ ወረርሽኝ ሳቢያ እስካሁን የ32 ሺኅ 548 ሰዎች ህይወት ሲያፍ 584 ሺህ 16 ሰዎች ደግሞ በኮቪድ -19 ተይዘዋል፡፡

በሌላ ዜና የኦክስፈርድ ዩኒቨርስቲ ከእንግሊዝ ውጪ ለሚያርገው የክትባት ሙከራ ተመራጯ ብራዚል ሳትሆን እንዳልቀረ እየተነገረ ነው፡፡

በዚህ የክትባት ሙከራ ከሁለት ከተሞች ሁለት ሺ ሰዎች የተመለመሉ ሲሆን መድሀኒቱን የኦክስፎርድ ዩኒቨርስቲና በሳኦ ፖሉ የሚገኘው መንግስታዊ ዩኒቨርስቲ በጋራ ያጋጁት መሆኑ ተነግሯል፡፡

ይህ መድሀኒት ከእንግሊዝ ውጪ ሲሰጥ ለመጀመሪያ ጊዜ ሲሆን በብራዚል የኮሮና ቫይረስ ወረሽኝ በከፋ ደረጃ ላይ ቢሆንም አሁንም ግን ያው እንቅስቃሴ እንደነበረ ነው፡፡

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን፣ዜናዎችን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ። https://t.me/ethiofm107dot8

በያይኔአበባ ሻምበል
ግንቦት 27 ቀን 2012 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.