ከዶናልድ ትራምፕ በሳል አመራር መጠበቅ የዋህነት ነው ሲሉ የቀድሞው የአሜሪካ መከላከያ ሚንስትር ጀምስ ማቲስ ተናገሩ ።

የቀድሞው ጀነራል ጦር ማቲስ ፕሬዘዳንቱ የጆርጅ ፍሎይድ ግድያ ዙሪያ የሰጡትን ምላሽ ክፉኛ ተችተዋል፡፡

ማቲስ እንደሚሉት ዶናልድ ትራምፕ ስልጣናቸውን እየገነቡ ነው አሜሪካዊያንን አንድ አድርጎ ሊመራ ሲገባ እርሱ ግን እየከፋፈለን ነው ብለዋል።

ቢቢሲ እንደሚለው ይህ የጄምስ ማቲስ ትችት ያልተለመደ ነው ፡፡

ጄኔራሉ ጄምስ ማቲስ ከዶናልድ ትራምፕ በሳል አመራር መጠበቅ የዋህነት ነው ሲሉ አክለዋል፡፡

ማቲስ የጆርጅ ፍሎይድን ግድያ ተከትሎ በመላው ሀገሪቱ የተስፋፋውን ተቃውሞ ለማርገብ ዶናልድ ትራምፕ የተከተሉት መንገድ አስቆጥቷቸዋል።

ጄኔራል ጄምስ በ2018 የሥልጣን መልቀቂያ ደብዳቤ ያስገቡት አሜሪካ ጦሯን ከሶሪያ ምድር እንድታስወጣ ፕሬዝዳንት ትራምፕ ድንገተኛ ውሳኔ ማስተላለፋቸውን በመቃወም ነበር።

ከዚያ ጊዜ በኋላ በፖለቲካዊም ሆነ ወታደራዊ ጉዳዮች ላይ የሰላ ትችት ሲዘሰነዝሩ ተደምጠው አያውቁም ነበር፡፡

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን፣ዜናዎችን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ። https://t.me/ethiofm107dot8

በያይኔአበባ ሻምበል
ግንቦት 27 ቀን 2012 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *