የአባ ሳሙኤል ከፍተኛ ጥበቃ ማረሚያ ቤት ለኮሮና ቫይረስ ተጠርጣሪ ታራሚዎች ለይቶ ማቆያ እንዲሆን ተደርጎ መዘጋጀቱ ተገለጸ።

በአዲስ አበባ የሚገኘው የአባ ሳሙኤል ከፍተኛ ጥበቃ ማረሚያ ቤት ለኮሮና ቫይረስ ተጠርጣሪ ታራሚዎች ለይቶ ማቆያ እንዲሆን ተደርጎ መዘጋጀቱ ተገለጸ።

የፌደራል ማረሚያ ቤቶች ኮሚሽን እንዳስታወቀው በኢትዮጵያ አስካሁን ድረስ በማረሚያ ቤቶች በኮሮና ቫይረስ የተጠቃ ታራሚ የሌለ ሲሆን በቀጣይ የቫይረሱ ተጠቂ ታራሚ ቢኖር በሚል የለይቶ ማቆያ ተዘጋጅቷል።

በኮሚሽኑ የህዝብ ግንኙነት ኮሚሽን ሃላፊ አቶ ገረመው አያሌው ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንዳሉት በየጊዜው ከህግ ታራሚዎች ላይ ናሙና እየተወሰደ የ“COVID 19“ ምርመራ እያደረገ ነው።

የፌዴራል ማረሚያ ቤት ኮሚሽን በአዲስ አበባ አቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ አባሳሙኤል ከፍተኛ ጥበቃ ማረሚያ ቤት የለይቶ ማቆያ ቦታ አዘጋጅቻለሁ ብሏል፡፡

ይህ የታራሚዎች ለይቶ ማቆያ ማዕከል የህክምና ቁሳቁስ እና ሌሎች የደህንነት ጥበቃ ስራዎች ተሰርተው መጠናቀቁንም ሃላፊው ተናግረዋል።

ምንም እንኳን እስካሁን በማረሚያ ቤቶች የኮረና ቫይረስ ኬዝ ባይኖርም ምናልባት ቢከሰት ተገቢውን ህክምና መስጠት እንዲቻል የለይቶ ማቆያ ቦታ ማዘጋጀቱን አቶ ገረመው ነግረውናል።

የኮሮና ቫይረስን ለመከላከል የሚያስችል የአፍና የአፍንጫ መሸፈኛ ጭንብል የህግ ታራሚዎች እያመረቱ ይገኛሉ ተብላል፡፡

የህግ ታራሚዎች ካመረቱት ጭንብል መካከል ዓለም አቀፍ የቀይ መስቀል ማህበር 26 ሺህ በመግዛት መልሰው ለፌዴራልና ለክልል ማረሚያ ቤቶች ማከፋፈላቸውን ሃላፊው ተናግረዋል።

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን፣ዜናዎችን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ። https://t.me/ethiofm107dot8

በሔኖክ ወ/ገብርኤል
ግንቦት 27 ቀን 2012 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *