የፕሪምየር ሊጉ ክለቦች የውድድር ዘመኑን ማጠናቀቅ ስለሚቻልባቸው የተለያዩ አማራጮች ላይ ለመምከር ዛሬ ይወያያሉ::

የፕሪምየር ሊጉ ክለቦች የውድድር ዘመኑን ማጠናቀቅ ስለሚቻልባቸው የተለያዩ አማራጮች ላይ ለመምከር ዛሬ ይወያያሉ ተጫዋቾች ባለፈው ሳምንት አካላዊ ንክኪን የሚፈቅድ ልምምድ መስራት ጀምሯል። ፕሪምየር ሊጉን በሰኔ አጋማሽ ከመጀመርም ታቅዷል። ዛሬ በሚደረገው ውይይት በዋናነት ከሚነሱ ጉዳዮች መካከል የውድድር ዘመኑን ሜዳ ላይ ማጠናቀቅ የማይቻልባቸው አጋጣሚዎች ከተፈጠሩ ምን ይደረግ የሚለው አንዱ ነው።

በዝርዝር እንደሚደረግ በተነገረው ውየየይይት ክለቦች በሙሉ የውድድር ዘመኑን ማጠናቀቅ ባይቻል እንዴት እልባት ይበጅለት በሚለው ላይ ሃሳብ እንዲያዋጡ ተጠይቀዋል። ወራጅ አይኑር የሚሉ ክለቦች ቢኖሩም ክለቦች የሚስማሙበት አይመስልም። እንደገና በሚጀመረው የውድድር ዘመን የሚደረጉ የመጀመሪያ ዙር ጨዋታዎች መርሃግብርም ማረጋገጫ እንደሚሰጠው ይጠበቃል። የጨዋታ መጀመሪያ ሰዓት እና የማሰራጫ መንገድም ለውይይት እንደሚቀርብ ተነግሯል። ክለቦች የማዳበሪያ ሃሳቦችን ይሰጡበታል።

የፕሪምየር ሊጉ ሁለት የመክፈቻ ጨዋታዎች በሰኔ 17 ይከናወናሉ። በሳምንቱ መጨረሻ ደግሞ ሙሉ መርሃግብሮች ይከናወናሉ። በጨዋታ እለት ሊተገበሩ የሚገባቸው ነገሮች እና ወደ ውድድር ለመመለስ የሚረዱ መመሪያዎች ይቀርባሉ። ክለቦችም ቢሆኑ ጥብቅ መመሪያዎችን ሲጥሱ የሚከተላቸውን መዘዝ እንዲያውቁት ይደረጋል። ቅጣት ሊጣልባቸው ይችላል። በስታዲየሞች ውስጥ እንዲገኙ የሚፈቀድላቸው ሰዎች ቁጥርም ከ300 እንዳይበልጥ ገደብ ተጥሎበታል ። የፕሪምየር ሊጉ ዋና ስራ አስፈጻሚ ሪቻርድ ማስተርስ ከቢቢሲ ስፖርት ጋር ባደረጉት ቆይታ የኮሮናቫ ቫይረስ ስርጭት ሁለተኛው ማዕበል ተከስቶ የውድድር ዘመኑ የሚሰረዝ ከሆነ ወራጅ ክለብ አይኑር የሚል ሃሳብ የሚያነሱ ወገኖች ሃሳባቸውን አቅርበው የሚከራከሩበት ትክክለኛው ጊዜ ነው ባይ ናቸው።

እንዲያም ሆኖ ሃሱቡ ተግባራዊ እንዲሆን የ14 ክለቦችን ድጋፍ ማግኘት ይጠበቅባቸዋል። የእግር ኳስ ማህበሩ ግን ሃሳቡን እንደሚቃወመው ተናግሯል። የእግር ኳስ አስተዳዳሪው አካል የራሱ የሆነ ከፍ ያለ ድምጽ አለው። የፕሪምየር ሊጉ ሃላፊዎች ግን ጨዋታዎችን ለሚያሰራጩ ተቋማት ከፍ ያለ ገንዘብ ከመመለስ አደጋ ጋር ላለመጋፈጥ የውድድር ዘመኑ ቢጠናቀቅ ይመርጣሉ። በጉዳዩ ዙሪያ ድምጽ እንደማይሰጥበት ግን ተነግሯል።

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን፣ዜናዎችን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ።

https://t.me/ethiofm107dot8

በአቤል ጀቤሳ

ግንቦት 27 ቀን 2012 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *