የ13 ዓመት የእንጀራ ልጁን አስገድዶ የደፈረው የ60 አመቱ አዛውንት በ11 ዓመት አስራት ተቀጣ።

ወንጀሉ የተፈጸመው በአማራ ክልል ማዕከላዊ ጎንደር ዞን ጠገዴ ወረዳ ሲሆን ጥር 21/2012 ዓ/ም ከቀኑ 7:00 አካባቢ ተከሳሽ ሰረበ ተገኘ አባቴ ብላ አምና ከጎኑ የሆነችውን የ13 አመት የእንጀራ ልጁን በሽጉጥ በማስፈራራት አስገድዶ እንደደፈራት የክስ ዝርዝሩ ያስረዳል።

ተጠርጣሪውም ለጊዜው ቢሰወርም በዳንሸ ከተማ መያዙም ተገልጿል።

የሶሮቃ ንዑስ ወረዳ ፖሊስ ምርመራውን አጣርቶ ለዓቃቤ ህግ አስተላልፏል ።

ዓቃቤ ህግም የተላለፈውን የወንጀል ህግ አንቀፅ 620/2/ሀ እና ለን በመጥቀስ ክስ መስርቷል ።

ክሱን የተመለከተው የሶሮቃ ንዑስ ወረዳ ፍርድ ቤት ተከሳሽን ጥፋተኛ በማለት ተከሳሽ እንዲከለከል ፍርድ ቤቱ ቢፈቅድም መከላከያ ማስረጃ ሊያቀርብ አልቻለም ።

ፍርድ ቤቱ የድርጊቱን አስነዋሪነት በመግለፅ ጥፋተኛነቱን በማሳየት የዓቃቤ ህግን አንድ ማክበጃ በመቀበል ተከሳሽ የ8 ልጆች አባት በመሆኑና ከአሁን በፊት ሪከርድ ባለመኖሩ ሁለት ማቅለያዎችን ፍርድ ቤቱ መያዙ ተገልጿል ።

ወንጀሉ እሱንም ሆነ ሌሎችን ያስተምራል በሚል ተከሳሽ እጁ ከተያዘበት ጀምሮ የሚታሰብ ግንቦት 21/2012 ዓ/ም በዋለው የወንጀል ችሎት በ11 አመት ፅኑ እስራት እንዲቀጣ እንደወሰነበት የጠገዴ ወረዳ ኮሙንኬሽን አስታውቋል።

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን፣ዜናዎችን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ። https://t.me/ethiofm107dot8

ኢትዮ ኤፍ ኤም የኢትዮጵያዊያን
ግንቦት 27 ቀን 2012 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *