ፔድሮ ሮማን ሊመርጥ እንደሚችል ተነግሯል

ፔድሮ በምዕራብ ለንደን ለአምስት ዓመት ከቆየ በኋላ አሁን ላይ ስለቀጣይ ማረፊያው እያሰበ ነው። ሮማ ደግሞ ቀዳሚው ማረፊያው ሊሆን እንደሚችል ተነግሯል።

ሮማ የ32 ዓመቱን ተጫዋች አጥብቆ እንደሚፈልገው ተነግሯል። በመጨረሻ ጥረቱ ፍሬ የሚያፈራ ይመስላል። ፔድሮ ባርሴሎናን ለቅቆ ቼልሲን የተቀላቀለው በ2015 ነበር። ለፕሪምየር ሊጉ ክለብ በ201 ጨዋታዎች ላይ ተሰልፎ መጫወትም ችሏል። ወደ ስታምፎርድ ከመጣ በኋላ የፕሪምየር ሊግ፣ ኤፍ ኤ ካፕ እና ዩሮፓ ሊግ ዋንጫዎችን አሸንፏል።

ከክለቡ ከመለያየቱ በፊት ቼልሲ ከቀዳሚዎቹ አራት ቡድኖች አንዱ ሆኖ እንዲጨርስ የራሱን አስተዋጽኦ ያበረክታል ተብሏል።

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን፣ዜናዎችን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ።

https://t.me/ethiofm107dot8

በአቤል ጀቤሳ

ግንቦት 27 ቀን 2012 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *