ማስተር ካርድ ፋውንዴሽን ከአፍሪካ በሽታ መቆጣጠር ማዕከል ጋር በመቀናጀት ኢትዮጵያን ጨምሮ ለቀሪ የአፍሪካ አገራት 1 ሚሊዮን የኮሮና ቫይረስ መመርመሪያ ኪት ሊሰጥ መሆኑን አስታውቋል።

ማስተር ካርድ ፋውንዴሽን ከአፍሪካ በሽታ መቆጣጠር ማዕከል ጋር በመቀናጀት ኢትዮጵያን ጨምሮ ለቀሪ የአፍሪካ አገራት 1 ሚሊዮን የኮሮና ቫይረስ መመርመሪያ ኪት ሊሰጥ መሆኑን አስታውቋል።

ፋውንዴሽኑ ለኢትዮ ኤፍ ኤም በላከው መግለጫ እንዳመለከተው በአፍሪካ እየተባባሰ የመጣውን የኮሮና ቫይረስ ለመከላከል 1 ሚሊዮን የመመርመሪያ ኪት እና ሌሎች የህክምና ቁሳቁሶችን ኢትዮጵያን ጨምሪ ለሌሎች የአፍሪካ አገራት ድጋፍ አደርጋለሁ ብሏል።

ከመመርመሪያ ኪት በተጨማሪም 10 ሺህ የማህበረሰብ ጤና ሰራተኞችን በኮሮና ቫይረስ መከላከያ ስራዎች ዙሪያ አሰልጥኖ በአገራቱ እንደሚያሰማራም አስታውቋል።

በአፍሪካ የኮሮና ቫይረስ ስርጭት በማህበረሰብ ደረጃ በመድረሱ ምክንያት የቫይረሱን ስርጭት ለመከላከል ፋውንዴሽኑ ከአፍሪካ በሽታ መከላከልና መቆጣጠር ጋር በመቀናጀት ማህበረሰቡ ታች ክፍል ድረስ በመግባት ምርመራ ማድረግ የሚያስችሉ ድጋፎችንም አደርጋለሁ ብሏል።

የአፍሪካ በሽታ መከላከልና መቆጣጠር ኢትዮጵያን ጨምሮ ለሌሎች የአህጉሪቱ አገራት ከ2 ነጥብ 5 ሚሊዮን የላብራቶሪ ቁሳቁሶች፣የህክምና መተንፈሻ መሳሪያዎች እና የኮሮና ቫይረስ ተጋላጭነተን መቀነስ የሚያስችሉ ቁሳቁሶችን ድጋፍ ማድረጉን ገልጿል።

በተጨማሪም ማዕከሉ በኢትዮጵያ እና በሌሎች 14 አገራት 164 የማህበረሰብ ጤና ባለሙያዎችን አገራቱ በኮሮና ቫይረስ መከላከል ስራዎችን እንዲያግዙ ማሰማራቱንም አስታውቋል።

የኢቦላ ቫይረስ ከ5 ዓመት በፊት በምዕራብ አፍሪካ አገራት በተከሰተበት ወቅት በሽታውን ለመቆጣጠር በመከላከያ መንገዶች እና የህክምና ምርመራ ጣቢያዎችን ማስፋት ትልቁ መሳሪያ እንደነበር የተገለጸ ሲሆን ኮሮና ቫይረስንም በተመሳሳይ መንገድ መከላከል እና መቆጣጠር እነደሚቻል ማዕከሉ ያምናል ለዚህ ደግሞ ድጋፍ ያደርጋል ተብሏል።

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን፣ዜናዎችን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ። https://t.me/ethiofm107dot8

በትግስት ዘላለም
ግንቦት 28 ቀን 2012 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *