በአዲስ አበባ በተለምዶ ቺቺንያ አካባቢ በወሲብ ንግድ ይተዳደሩ የነበሩ 120 ሴተኛ አዳሪዎችን ወደ መልሶ ማቋቋሚያ ማዕከል መግባታቸው ተገለጸ።

የአዲስ አበባ ከተማ የሰራተኛ እና ማህበራዊ ቢሮ ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንዳስታወቀው በከተማዋ በተለምዶ ቺቺኒያ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ በወሲብ ንግድ ተሰማርተው የነበሩ 120 ሴተኛ አዳሪዎችን ወደ መልሶ ማቋቋም ማዕከል ማስገባቱን ተናግሯል፡፡

በአጠቃላይ በሰራተኛና ማህበራዊ ቢሮ የተለዩ 11 ሺህ ሴተኛ አዳሪዎች በከተማዋ እንደሚገኙ የቢሮው ሃላፊ አቶ ሙሉጌታ ተፈራ ተናግረዋል፡፡

በቀጣይ እነዚህን ሴቶች ወደ ማዕከል ለማስገባት ከተለያዩ ግብረሰናይ ድርጅቶች ጋር በቅርበት እየሰራ እንደሚገኝ ቢሮው አስታውቋል፡፡

ከእነዚህም ውስጥ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸውን ሴቶች ኤልሻዳይ ከሚባል ግብረሰናይ ድርጅት ጋር በመተባበር በመሆን ወደ መልሶ ማቋቋም ማዕከል ለማስገባት ቅድመ ስራ መሰራቱን ነው የተገለፀው፡፡

ቢሮው እነዚህን ሴቶች ወደ ማዕከል የሚያስገባው ከዚህ ህይወት ወጥተው ራሳቸውን እንዲችሉ ለማድረግ ነው ትብሏል፡፡

በተጨማሪም እነዚህ ዜጎች ከወቅቱ የኮሮና ቫይረስ ለመታደግ እነደሆነም ቢሮው ገልጿል።

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን፣ዜናዎችን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ። https://t.me/ethiofm107dot8

በሔኖክ ወ/ገብርኤል
ግንብት 28 ቀን 2012 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.