በአፍሪካ በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሰዎች ቁጥር ከ160 ሺህ ተሻግሯል፡፡

የአፍሪካ በሽታዎች ቁጥጥርና መከላከል ማእከል ሲ ዲ ሲ ትናንት እንዳስታወቀው በአፍሪካ ምድር 162 ሺህ 673 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው በምርመራ ተረጋግጧል፡፡

እንደ ማእከሉ መረጃ በቫረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር ረቡእ እለት ከነበረበት 158 ሺህ 318 ነው በአንድ ቀን ልዩነት ውስጥ ትናንት ወደ 162 ሺህ 673 ከፍ ያለው፡፡

በአህጉሪቷ የሟቾች ቁጥርም ረቡእ እለት 4ሺህ 508 የነበረ ሲሆን ትናንት 4ሺህ 601 ደርሷል፡፡

የወረርሽኙ ስርጭት በ54ቱም የአህጉሪቷ ሃገራት መሰራጨቱን የሚናገረው ሲዲሲ፤ 70 ሺህ 475 ደግሞ ከህመማቸው ማገገማቸውን ገልጧል፡፡

ደቡብ አፍሪካ፣ግብጽ፣ናይጄሪያ፣አልጄሪያ ጋና እና ሞሮኮ ወረርሽኙ በስፋት ጉዳት ያደረሰባቸው ቀዳሚዎቹ የአፍሪካ ሃገራት ናቸው፡፡

የሰሜን አፍሪካ ቀጠና በበሽታው የተያዙ ሰዎች ቁጥርም ይሁን የማቾች ቁጥር ከፍተኛ ሆኑ የተመዘገበበት ነው፡፡

እንደ ሲዲሲ መረጃ ደቡባዊው የአፍሪካ ክፍል በቫይረሱ ስርጭት እየተፈተነ ያለ ሁለተኛው ቀጠና ሲሆን ምዕራብ አፍሪካ ደግሞ በሶስተኛነት እንደሚከተል ሲጂቲኤን ዘግቧል።

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን፣ዜናዎችን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ። https://t.me/ethiofm107dot8

በዳንኤል መላኩ
ግንቦት 28 ቀን 2012 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.