ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ በተደረገው 5798 የላብራቶሪ ምርመራ አንድ መቶ ስልሳ ዘጠኝ (169) ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ተገኝቶባቸዋል፡፡

በአጠቃላይ በሀገራችን ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 1805 ደርሷል፡፡

ከኮሮና ቫይረስ ጋር በተገናኘ የአንድ የ35 ዓመት ሴት ኢትዮጵያዊ ህይወት አልፏል።

ለአስክሬን ምርመራ በሆስፒታል በተደረገ ምርምራ የኮሮና ቫይረስ ተገኝቶባታል።

በአጠቃላይ በሀገራችን ቫይረሱ የተገኘባቸው እና ህይወታቸው ያለፈ ሰዎች ቁጥር አስራ ዘጠኝ (19) ደርሷል፡፡

የጤና ሚኒስቴርና የኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት በህልፈተ ህይወታቸው የተሰማቸውን ሀዘን እየገለጹ ለቤተሰቦቻቸው መፅናናትን ይመኛል፡፡

በሌላ መልኩ በትላንትናው ዕለት አስራ ሁለት (12) ሰዎች (10 ከአማራ ክልል እና 2 ከቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል) ያገገሙ ሲሆን በአጠቃላይ በሀገራችን ከበሽታው ያገገሙ ሰዎች ቁጥር 262 ነው።

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *