“ሊቨርፑል ቨርነርን በማጣት ሊቆጭ አይገባም” ሮቢ ፎውለር

የሊቨርፑል ታሪካዊ ተጫዋች ሮቢ ፎውለር የቀድሞ ክለቡ ቲሞ ቨርነርን በማጣቱ የሚያጣው ነገር አለመኖሩን ተናግሯል። ጀርመናዊው ለወራት ወደ አንፊልድ እንደሚያመራ ሲነገር ሰንብቶ ቼልሲን እንደሚቀላቀል ተረጋግጧል።

ፎውለር ሚረር ላይ ባወጣው ጽሁፍ ” ከሰሞኑ ከቨርነር ጋር የተያያዘ ወሬ በስፋት ሲወራ ነበር። እውነት ለመናገር እኔ በግሌ የእርሱ አድናቂ አይደለሁም” ብሏል። “የትልቅ ተሰጥኦ ባለቤት አንደሆነ ይገባኛል። በጨዋታዎች ላይ ልዩነት መፍጠር የሚያስችሉ አጋጣሚዎችን ሜዳ ላይ ተመልክተናል ይህም ብቃቱን ያሳያል ።

“ልብ ልንለው የሚገባ አንድ ሃቅ አለ። ቨርነር ከሊቨርፑል ሶስቱ የፊት መስመር ተሰላፊዎች ጋር በሚነጻጸር ደረጃ ላይ ይገኛል ? ለእኔ ምላሹ በጭራሽ የሚል ይሆናል። “አንዳንዶች ስለ እርሱ የሚያወሩበት መንገድ ማርኮ ቫን ባስተንን የሆነ ያስመስለዋል። ወደ የትኛውም ቡድን ተቀላቅሎ የሚሳካለት አይነት ያደርጉታል።

” በጨዋታዎች ላይ በቋሚነት ተጽዕኖ ማሳረፍ ይችላል? እኔ እንደዚያ አይታየኝም። እንዲፎካከራቸው እና እንዲተካቸው ከታሰቡት ተጫዋቾች ጋር ይስተካከላል በሊቨርፑል ይህንን ማድረግ አይችልም። ምናልባት በቼልሲ ዕድል ይኖረው ይሆናል። “

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን፣ዜናዎችን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ።

https://t.me/ethiofm107dot8

በአቤል ጀቤሳ

ሰኔ 1 ቀን 2012 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *