ባርሴሎና ከኢንተር ሚላን ጋር በላውታሮ ማርቲኔዝ ዝውውር ዙሪያ እያደረገ ያለው ድርድር እጅግ ዘግይቷል። እናም ዓይኑን ወደ ሌሎች ሊጎች እያማተረ ነው ። አርሰናል እና ኦባሜያንግ ደግሞ ዋነኞቹ ዒላማዎቹ ሆነዋል ።
የኮንትራት ዘመኑ ሊጠናቀቅ የሚቀረው የአንድ ዓመት ጊዜ ብቻ ነው። አዲስ ኮንትራት የመፈራረም ፍላጎት እንደሌለው በተደጋጋሚ አሳይቷል። መድፈኞቹ የተወሰነ ገንዘብ ሊያገኝ ይፈልጋል። ማርካ ይዞት የወጣው ዜና በመደፈኞቹ ቤት በአጥቂው እና በክለቡ የስራ ሃላፊዎች መካከል የተፈጠረውን አለመግባባት ተከትሎ ባርሴሎና የላውታሮ ማርቲኔዝን ጉዳይ ወደጎን ብሎ ፊቱን ወደ አርሰናሉ አጥቂ እንዲያዞር ሊያደርገው እንደሚችል ለኢንተር ሚላን ሃላፊዎች ተናግሯል።
ኢንተር ሚላን በላውታሮ ማርቲኔዝ የውል ማፍረሻ ላይ ሰፍሮ የሚገኘውን 111ሚ.ዩ ባርሴሎና እንዲከፍል ይፈልጋል ። ባርሴሎና የተወሰኑ ወራት ከጠበቀ ግን ኦባሜያንግን በ25 ሚ.ዩ ማግኘትይችላል።
ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን፣ዜናዎችን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ።
በአቤል ጀቤሳ
ሰኔ 1 ቀን 2012 ዓ.ም











