አየር መንገዱ ወደ 29 ከተሞች በረራ እንደሚጀምርና የትራንዚት አገልግሎቱንም እንደሚጀምር ነው ያስታወቀው።
የተባበሩት አረብ ኢምሬትስ ፌዴራል መንግስት እንዳስታወቀው ፤ በኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ስጋት ምክንያት ኢምሬትስ አየር መንገድ የመንገደኞች በረራ አገልግሎት እንዳይሰጥ ተላልፎ የነበረው እገዳ ተነስቷል፡፡
ከፈረንጆቹ ሰኔ 15 ጀምሮ በቦይንግ 777-300ER አውሮፕላኖቹ ወደ ተጨማሪ 16 ከተሞች መንገደኞችን ማጓጓዝ እንደሚጀምር አስታውቋል፡፡
በተጨማሪም ወደ ተለያዩ ሃገራት ጉዞ የሚያደርጉ መንገደኞች በሃገሪቷ ትራንዚት እንዳያደርጉ ተላልፎ የነበረው እገዳ መነሳቱ ነው የተነገረው፡፡
አየር መንገዱ በረራውን የሚጀምረው ወደ ባህሬን፣ማንችስተር፣ዙሪክ፣ቬና ፣ አምስተርዳም ፣ ኮፐንሃገን፣ ደብሊን፣ ኒውዬርክ ፣ሲኡል፣ ዋላላንፑር፣ ሲንጋፑር፣ ጃካርታ፣ ታይፔ፣ሆንግ ኮንግ፣ፐርዝና ብሪስቤን ከተሞች ነው፡፡
በተጨማሪም ከዛሬ ጀምሮ ፓኪስታን በሚገኙ የኢምሬትስ መዳረሻዎች ካራቺ፣ላሆሪ እና ኢስላማባድ በረራዎችን ያቀርባል፡፡
አየር መንገዱ ለመንገደኞቹ ጤንነት ተገቢውን ጥንቃቄ እንደሚያደርግም አስታውቋል፡፡
ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን፣ዜናዎችን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ። https://t.me/ethiofm107dot8
በአባይነሽ ሽባባው
ሰኔ 1 ቀን 2012 ዓ.ም











