ስፖርት

የሊቨርፑሉ ከንቲባ በአንፊልድ የሚደረጉ ጨዋታዎች ላይ ቅሬታ እንደሌለባቸው ተናገሩ

የሊቨርፑሉ ከንቲባ ጆ አንደርሰን ሊቨርፑል ጨዋታውን አንፊልድ ላይ ማከናወን የለበትም ። በጉዲሰን ፓርክ የሚከናወነው የሜርሲ ሳይድ ደርቢም ወደ ሌላ ስታዲየም ቢዘዋወር እመርጣለሁ ሲሉ ከዚህ ቀደም የሰነዘሩትን ሃሳብ ማጠፋቸውን ተናግረዋል።

አንደርሰን ከዚህ ቀደም ሃሳቡን የተቃወሙት የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ አስጊ በሆነበት በዚህ ወቅት አንፊልድ እና ጉዲሰን ፓርክ አካባቢ ቁጥሩ ከፍ ያለ ህዝብ ሊሰበሰብ ይችላል ብለው በመስጋታቸው ነበር። ፕሪምየር ሊጉ በመጪው ሰኔ 17 ይጀመራል ።

ከዚያ በፊት ዛሬ ሊቨርፑል ከኤቨርተን የሚያደርገው ጨዋታ የሚከናወንበት ሜዳ ይወሰናል። ሊቨርፑል ከሜዳ ውጪ ከኤቨርተን እና ማንቸስተር ሲቲ የሚያደርጋቸው ጨዋታዎች ከመጀመሪያዎቹ 32 ጨዋታዎች በገለልተኛ ስታዲየም ሊከናወኑ የሚችሉ ብቸኞቹ ጨዋታዎች ናቸው። የሜርሲ ሳይድ ደርቢ የሚከናወንበት ቦታ ዛሬ ውሳኔ ያገኛል። የሊቨርፑል ከተማ አስተዳደር ሸንጎ አማካሪ ቡድን ጨዋታው በጉዲሰን ፓርክ ይከናወን ወይስ ወደ ገለልተኛ ስታዲየም ይዘዋወር በሚለው ሃሳብ ላይ ይመክራል።

የውድድር ዘመኑ በሰኔ 17 ሲጀመር ከሚደረጉ ጨዋታዎች በአንዱ ማንቸስተር ሲቲ በአርሰናል ከተሸነፈ በደርቢው ጨዋታ ሊቨርፑል ድል ከቀናው ከ30 ዓመት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ የፕሪምየር ሊግ ዋንጫውን ማንሳቱን ያረጋግጣል።። አንደርሰን “ዛሬ ላይ ከአራት ሳምንት በፊት ከነበርንበት በተሻለ ሁኔታ ላይ እንገኛለን ” ብለዋል። “በስታዲየም ዙሪያ መሰብሰብ የሚያስከትለውን ችግር በሚገና ለደጋፊዎች አስተላልፈናል ” ሲሉም ያክላሉ።

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን፣ዜናዎችን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ።

https://t.me/ethiofm107dot8

በአቤል ጀቤሳ

ሰኔ 1 ቀን 2012 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *