የኢትዮጵያ የወጪ ንግድ በኮሮና ቫይረስ ወቅት ማደጉን ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ተናገሩ።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ዛሬ በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ለምክር ቤት አባላት ማብራሪያ ሰተዋል፡፡

ከ2007 ጀምሮ እስከ አምና ድርስ እያሽቆለቆለ የነበረውን የወጪ ንግድ እድገት መንግስት ለማሻሻል ጥረት ማደረጉን ያነሱት ጠቅላይ ሚኒስትሩ በተለይ የግብርና ምርቶችን በከፍተኛ መጠን ወደ ውጪ ለመላክ መቻሉን አስታውቀዋል፡፡

ባለፉት አስር ወራትም የወጪ ንግድ እድገቱ 13 በመቶ እድገት ማስመዘገቡን አንስተው ይህንን እድገት እንዲፈጥን ካደረጉት አንዱ ደግሞ ኮሮና ቫይረስ ነው ብለዋል፡፡

ሀገሪቱ ባለፊት 10 ወራት 667 ሚሊንዮ ዶላር ያለው ቡናን ወደ ውጪ ልካለች እድገቱም አስራ ስድስት በመቶ ነው፡፡

ለዚህ እድገት ምክንያት ደግሞ ፍላጎት እና የዋጋ ጭማሪ ማሳየቱን ጨምሮ ከዚህ በፊት ቡናን ያርቱ የነበሩ ሀገራት በበቂ ሁኔታ ወደ ገበያው አለመግባታቸው መሆኑን ይናገራሉ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ፡፡

በኮሮና ቫይረስ ወረሽኝ ምክንያት የጎረቤት ሀገራት የአበባ ዘርፋ ከፍተኛ ችግር እንደደረሰበት አስታውሰው ኢትዮጵያ ግን ባለፉት 10 ወራት 440 ሚሊየን ዶላር ምርት ወደ ውጭ አገራት መላኩን ተናግረው እድገቱም 84 በመቶ ነው ብለዋል፡፡

ሌላው ከፍተኛ እድገት ከታየበት ውስጥ የስጋ ምርት አንዱ ሲሆን 45 ሚሊየን ዶላር የሚያወጣ ምርት ወደ መካከለኛው ምስራቅ ሀገራት መላኩን እና እድገቱም 21 በመቶ መጨመሩን ይናገራሉ፡፡

እንዲያውም ጥራት ያለው የስጋ ፍላጎት በተለይ በመካከለኛው ምስራቅ ሀገራት በመንግስታት ደረጃ ጥያቂ እየቀረበ መሆኑን አንስተዋል፡፡

በኮሮና ቫይረስ ምክንያት መጠኑ ይለያይ እንጂ እንደ ቱሪዝም ያሉ እና ከእርሱ ጋር ተያያዥነት ያላቸው የአገልግሉት መስጫ ሆቴሎች ችግር እንዳገጠማቸው ተናግረው የትራንስፐፖርቱም ዘርፍ ከጉዳት አልተረፈም ብለዋል፡፡

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን፣ዜናዎችን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ። https://t.me/ethiofm107dot8

በያይኔአበባ ሻምበል
ሰኔ 1 ቀን 2012 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.