በአማራ ክልል ሰሜን ወሎ ዞን ራያ ቆቦ ወረዳ አመራሮች ላይ የግድያ ወንጀል የፈፀመው ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የአማራ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ።

ግንቦት 23/2012 ዓ.ም ህግ በማስከበር ላይ የነበሩ የራያ ቆቦ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ እና የወረዳው የህዝብ ሰላምና ደህንነት ጽ/ቤት ኃላፊ በነበሩት አመራሮች ላይ የግድያ ወንጀል ፈፅመው መሰወራቸውን ይታወቃል።

ሆኖም የአካባቢው የፀጥታ ኃይል ከነዋሪዎች ጋር ተቀናጅተው በመስራት 01/10/2012 ዓ.ም በቁጥጥር ስር ውለው አስፈላጊው ምርመራ እየተጣራ እንደሚገኝ ኮሚሽኑ አስታውቋል።

ወንጀሉ ከተፈፀመበት ጊዜ ጀምሮ የፀጥታ ኃይሉና የአካባቢው ማህበረሰብ ተጠርጣሪዎች እንዲያዙ ላደረጉት ያላሰለሰ ጥረት የሰሜን ወሎ ዞን ፖሊስ መምሪያ ኃላፊ ኮማንደር ተመስገን ቢረሳው ምስጋና አቅርበዋል።

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን፣ዜናዎችን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ። https://t.me/ethiofm107dot8

ኢትዮ ኤፍ ኤም የኢትዮጵያዊያን
ሰኔ 2 ቀን 2012 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.