በአውሮፓ የእንቅስቃሴ ገደብ መጣሉ ከ3 ሚሊየን በላይ ሰዎችን ከሞት ታድጓል ተባለ፡፡

በአውሮፓ የእቅስቃሴ ገደብ መጣሉ ከ3 ሚሊየን በላይ ዜጎችን በኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት ከሚከሰት ሞት መታደጉን አንድ ጥናት አስታወቀ፡፡

ከለንደን ኢምፔሪያል ኮሌጅ የወጣው ጥናታዊ ሪፖርት እንደሚያላክተው የእቅስቃሴ ገደብ እርምጃዎች በአፋጣኝ ባይወሰዱ ኖሮ በአውሮፓ የሟቾች ቁጥር ከዚህም የከፋ ይሆን ነበር፡፡

አሁንም ቢሆን ወረርሽኙ በአውሮፓ ሀገራት ገና መጀመሩ ነው እና የበርካቶችን ህይወት ሳያሳጣ ጥንቃቄ ማድረግ እንደሚገባም አጥኝዎቹ አስጠንቅቀዋል፡፡

እስካለፈው የአውሮፓውያኑ ግንቦት ወር ድረስ በእንቅስቃሴ ገደቡ ምክንያት የደረሱ ተፅዕኖችንም ለመዳሰስ የሞከረው ጥናቱ በእንቅስቃሴ ገደቡ ወቅት ብቻ በ11 የአውሮፓ ሀገራት 130ሺ ሰዎች በቫይረሱ ምክንያት መሞታቸውን አስታውቋል፡፡

የአውሮፓ ሀገራት ፈጠን ብለው የእቅስቃሴ ገደቡን ባይጥሉ ፣የንግድ እንቅስቃሴዎች እንዲቆሙ እና ሰዎች በቤታቸው እንዲቆዩ ባያደረግ ኖሮ እስከ አውሮፓውያኑ ግንቦት 4 ቀን ድረስ ባለው ጊዜ ውስጥ 3 ነጥብ 2 ሚሊየን ሰዎች በ11 ዱ የአውሮፓ ሀገራት ብቻ ሊሞቱ ይችሉ እንደነበር ጥናቱ በመላምት አስቀምጧል፡፡

የእንቅስቃሴ ገደቡ በሚሊየን የሚቆጠሩ ሰዎችን ከመቶ ታድጓል አውነት ይህ ሁሉ ሞት ተከስቶ ቢሆን ኖሮ ዓለማችን ከባድ የሚባለውን አሳዛኝ ክስተት ታስተናግድ ነበር ሲሉ አጥኚዎቹ መናገራቸውን ቢቢሲ ዘግቧል፡፡

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን፣ዜናዎችን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ። https://t.me/ethiofm107dot8

በትግስት ዘላለም
ሰኔ 2 ቀን 2012 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *