የቱርክ ፕሬዝዳንት በሊቢያ ጉዳይ ላይ ከአሜሪካው ፕሬዝዳንት ጋር መስማማታቸውን ተናገሩ፡፡

የቱርኩ ፕሬዝዳንት ጣይብ ኤርዶአን በሊቢያ ያለውን ቀውስ ተከትሎ ከአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራንፕ ጋር በስልክ መወያየታቸውን እና በአንዳንድ ጉዳዮች ላይ ከስምምነት መድረሳቸውን አስተውቀዋል፡፡

ቱርክ በዓለም አቀፍ ደረጃ ተቀባይነት ያለውን ገዢውን የፋይዝ አል ሴራጅ መንግስት እና በተባበሩት አረብ ኤምሬትስ፣ግብፅ እና ሩሲያ በሚደገፈው የካሊፍ ሀፍታር ሀይል በዋና ከተማዋ ትሪፖሊ ላይ በተደጋጋሚ ጥቃትን እያስተናገደ ያለው ይህንኑ መንግስት ትደግፋለች፡፡

ይህንንም ተከትሎ የቱርኩ ፕሬዝዳንት ከትራምፕ ጋር ባደረጉት የስልክ ውይይት በሊቢያ ያለውን ቀውስ ተከትሎ በአንዳንድ ጉዳዮች ላይ ከስምምነት ደርሰናል ብለዋል፡፡

የተስማሙበትን ጉዳይ ግን በግልፅ ለመገናኛ ብዙሀን አለማሳወቃቸውን ሮይተርስ ዘግቧል፡፡

ከዋይት ሀውስ የወጣው መረጃ እንደሚያሳየውም ፕሬዝዳንቶቹ ከሊቢያ ጉዳይ ባለፈ በአጠቃላይ የሰሜን አፍሪካ ሀገራትን ጨምሮ በሶሪያ እንዲሁም በሌሎችም አካባቢዎች ባሉ ቀውሶች ላይ መወያየታቸውን በደፈናው ተገልጿል፡፡

በአፍሪካ ጠንካራው እና ከውጭ ጣልቃ ገብነት ሙሉ ለሙሉ ነጻ የሆነ አስተዳድር የነበራቸው የሊቢያው መሪ ጋዳፊ መንግስታቸው በዲሞክራሲ ሰበብ ከፈራረሰ በኋላ ሊቢያ የአለማችን ወንበዴዎች መፈንጫ ሆናለች።

ሊቢያውያን በዲሞክራሲ ጥያቄ ስም ወደ አደባባይ እንዲወጡ ከኋላ ድጋፍ ያደርጉ የነበሩት ምዕራባዊያን ደግሞ አሁን ላይ ለሁለቱም ተፋላሚ ወገኖች የጦር መሳሪያ እየሸጡ በማዋጋት በጎን ደግሞ የሊቢያን ድፍድፍ ነዳጅ በመቀራመት ላይ ይመስላሉ።

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን፣ዜናዎችን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ። https://t.me/ethiofm107dot8

በትግስት ዘላለም
ሰኔ 2 ቀን 2012 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.