የግል ሆስፒታሎች እና ክሊኒኮች በኮሮና ቫይረስ ስጋት ምክንያት በመዘጋት ላይ መሆናቸውን ተገለፀ።

የኢትዮጲያ ጤና ክብካቤ ፌዴሬሽን ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንዳስታወቀው፤ ህብረተሰቡ በዚህ ሰእት ለመደበኛ የህክምና አግልግሎት ወደ ጤና ተቋማት የመሄድ ልምዱ ቀንሷል።

በዚህም ምክንያት ተቋማቱ አግልግሎት እየሰጡ አይደለም።

ከሆስፒታልና ጤና ጣቢያዎች በተጨማሪ የህክምና ግብአት አቅራቢዎችም ከገበያ ውጪ እየሆኑ በመምጣታቸው ለህንፃ ኪራይና ለሰራተኛ ደሞዝ ለመክፈል ተቸግረዋል ነው የተባለው።

በመሆኑም በርካቶቹ ተቋማት እንደሚዘጉ ማህበራችን ያውቃል ብለዋል፤ የፌዴሬሽኑ ፕሬዘዳንት ዶ/ር ማርቆስ ፈለቀ።

እናም መንግስት ልክ እንደሌሎች ሃገራት ለዘርፉ ድጋፍ ሊያደርግ ይገባል ነው ያሉት።

የግል የህክምና ተቋማት ከ40 እስከ 50 በመቶ የሚሆነውን የሃገሪቷን የህክምና ፍላጎት እንደሚሸፍኑ መንግስት ራሱ ያምናል የሚሉት ዶ/ር ማርቆስ፤ በአፋጣኝ መፍትሄ ካልተሰጥው ችግሩ የከፋ ይሆናል ብለዋል።

የመዘጋት አደጋ የተጋረጠባቸው የግል የህክምና ተቋማት በቁጥር ምን ያክል ይሆናሉ ስንል ላነሳንላቸው ጥያቄ ፤ይህን በትክክል ለመግለፅ ዝርዝር ጥናት ቢጠይቅም ወቅታዊ ሁኔታው ተፅእኖ ያላሳረፈበት የግል የህክምና ተቋም አለ ለማለት ይከብዳል ሲሉ መልሰውልናል።

የተዘጉ የግል ህክምና ተቋማት እንዳሉ አውቃለሁ ያሉን ዶክተር ማርቆስ አሁን ላይ ስማቸውን በተለያዩ ምክንያቶች ከመንገር ተቆጥበዋል።

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን፣ዜናዎችን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ። https://t.me/ethiofm107dot8

በአባይነሽ ሽባባው
ሰኔ 2 ቀን 2012 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *