ተጨማሪ 170 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ተገኘባቸው የ 3 ሰዎች ሕይወት አልፏል።

በኢትዮጵያ ባለፉት 24 ሰዓት በተደረገ 6187 የላቦራቶሪ ምርመራ ተጨማሪ 170 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ እንደተገኘባቸው እና የሶስት ሰዎች ሕይወት ማለፉን የጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰ አስታወቁ።

በዚህም እስካሁን በሀገሪቱ ቫይረሱ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 2506 ደርሷል።

ሚኒስትሯ እንደገለፁት ቫይረሱ እንደተገኘባቸው የተረጋገጠው እድሜያቸው ከ 2 እስከ 115 ዓመት ነው፡፡

በምርመራ ከተረጋገጠው 93 ወንድና 77 ሴቶች ሲጎኑ ሁሉም ኢትዮጵያውያን ናቸው።

ቫይረሱ የተገኘባቸው ሰዎች 81 ሰዎች ከአዲስ አበባ ሲሆኑ፣57 ሰዎች ከሶማሌ ክልል፤13 ሰዎች ከአማራ ክልል ፤7 ሰዎች ከትግራይ ክልል እና ከኦሮሚያ 7 ሰዎች፤ 3 ከሐረሪ እና 2 ሰዎች ከደቡብ ክልል ናቸው፡፡

በአጠቃላይ ቫይረሱ ተገኝቶባቸው በለይቶ ህክምና ውስጥ ያሉ ሰዎች 2068 ናቸው።

ተጨማሪ 22 ሰው ከበሽታው ያገገሙ ሲሆን በአጠቃላይ 401 ሰዎች ከበሽታው አገግመዋል።

እስካሁን በቫይረሱ ምክንያት የ 35 ሰዎች ህይወት አልፏል።

ሰላሳ ሶስት ሰዎች በጽኑ ህክምና ክፍል ክትትል እየተደረገላቸው መሆኑም ታውቋል።

እስካሁን በኢትዮጵያ አጠቃላይ 158 ሺህ 521 የላቦራቶሪ ምርመራ ተከናውኗል።

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን፣ዜናዎችን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ። https://t.me/ethiofm107dot8

ኢትዮ ኤፍ ኤም የኢትዮጵያውያን
ሰኔ 3 ቀን 2012 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.