ከቱኒዝያ ወደ ጣልያን ስደተኞችን ጭና ስትጓዝ በነበረች ጀልባ በደረሰ የመገልበጥ አደጋ የ 20 ሰዎች ህይወት አለፈ፡፡

ከቱኒዚያ የባህር ዳቻ በመነሳት ከ50 በላይ የአፍሪካ ስደተኞችን ጭና በነበረችው ጀልባ ላይ በደረሰ አደጋ 20 የሚሆኑ አፍሪካዊያን ስደተኞች ሊሞቱ መቻላቸውን ሮይተርስ ዘግቧል።

አስክሬኖቹ በባህር ዳርቻዎች አቅራቢያ ላይ መገኘታቸውን የተናገሩት ባስልጣናቱ ተጓዥ ስደተኞች መዳረሻቸውን ጣሊያን ለማድረግ ጉዞ በማድረግ ላይ ሳሉ አደጋው መፈጠሩን አስታውቀዋል፡፡

ይህንና እነዚህ ሟች ስደተኞች አፍሪካዊያን ናቸው ከመባሉ ውጪ የየት አገር ዜጎች እንደሆኑ እስካሁን አልታወቀም።

የባህር አድን ሰራተኞችም በመርከቧ ተጭው የነበሩ ሰዎችን የማፈላለግ ስራ መቀጠላቸው ተነግሯል፡፡

ተመሳሳይ አደጋዎችን የሚያስተናግደው ይህ የባሃር ዳርቻ ከሶስት ወር በፊት ስደተኞችን ጭና ከሊቢያ ወደ አውሮፓ ትጓዝ የነበረች ጀልባ ተገልብጣ የ86 ሰዎች ህይወት ማለፉ አይዘነጋም።

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን፣ዜናዎችን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ። https://t.me/ethiofm107dot8

በየውልሰው ገዝሙ
ሰኔ 3 ቀን 2012 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.