ጣልያናዊያን በኮሮና ቫይረስ ለሞቱ የእስልማና እምነት ተከታዮች የመቃብር ቦታ እጥረት ገጥሞናል አሉ።

በኮሮና ምክንያት ህይዎታቸውን ያጡ ጣልያናዊያን ሙስሊሞች ቁጥር ከፍተኛ መሆኑን ተከትሎ የመቃብር ስፍራ እጥረት ገጥሞናል ሲሉ የእምነቱ ተከታዮች ተናግረዋል፡፡

የኮሮና ቫይረስ በጣልያን ምድር ባደረሰው የከፋ ቀውስ በርካታ የሙስሊም ዕምነት ተከታዮች መሞታቸውን ዘገባው አስፍሯል፡፡

የሚላን ሴስቶ መስጊድ ኢማም አብዱላሂ ለአጃንስ ፍራንስ ፕረስ ሲናገሩ የሞቱትን ዘመዶቻቸውን የሚቀብሩበት ቦታ ያጡ ወገኖችን መመልከት ልብ ይሰብራል ብለዋል፡፡

የኮሮና ቫይረስ በጣልያን ምድር ብቻ ከ34 ሺህ በላይ ዜጎችን ህይዎት ቀጥፏል፡፡

በአገረ ጣልያን 2.6 ሚሊዮን የሙስሊም እምነት ተከታዮች እንደሚገኙ የሚነገር ሲሆን ይህም 4.3 በመቶ የሚሆነውን የአገሪቱን የህዝብ ቁጥር ይሸፍናሉ ሲል ቢቢሲ ዘግቧል፡፡

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን፣ዜናዎችን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ። https://t.me/ethiofm107dot8

በአባቱ መረቀ
ሰኔ 3 ቀን 2012 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *