ማስተር ካርድ ፋውንዴሽን በኢትዮጵያ በችግር ውስጥ ለሚገኙ ኢንተርፕራይዞች ድጋፍ እንደሚያደርግ አስታወቀ።

ፋውንዴሽኑ ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንዳስታወቀው በኮቪድ 19 ምክንያት ገበያቸው ችግር ውስጥ ለሚገኙ 11 አነስተኛ እና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች 3.2 ሚሊዮን ዶላር የሚገመት ድጋፋ አደርጋለሁ ብሏል።

ይህ ድጋፍ ድርጅቶቹ የኮሮና ቫይረስ መከላከያ ቁሳቁሶችን እንዲያመርቱ ያለመ መሆኑም ተነግሯል ፡፡

የማስተር ካርድ ፍውንዴሽን የኮሮና ቫይረስ በአፍሪካ እያደረሰ ያለውን ጫና ለመከላከል እየሰራሁ ነውም ብሏል፡፡

ድጋፍ የሚደረግላቸው 11 የንግድ ድርጅቶች ከ1ሺህ 60 በላይ ሠራተኞች እንዳሏቸው የተገለፀ ሲሆን ድጋፉ ሠራተኞቹ ከስራ ገበታቸው እንዳይቀነሱ ይረዳል ነው የተባለው፡፡

ከዚህ በተጨማሪም ድርጅቶቹ ምርታቸውን በኦንላይን እንዲገበያዩ የሚያስችል ድጋፍ እንደሆነም በኢትየጵያ የማስተር ካርድ ፋውንዴሽን ኃላፊ አቶ አለማየሁ ኮንዴ ተናግረዋል፡፡

ድጋፋ የተደረገላቸው ኢንተርፕራይዞችም ኤንዚሹዊዝ ፣ፊፍ ትሬዲንግ ፣ጋቤር ቴክስታይልስ፣ ሀብቴ ጋርመንት፣ ካበና ሌዘር፣ ኮትኬት ሌዘር፣ ማፊ ፣ሜሮን አዲስ አበባ፣ ሳዱላ ቢዝነስ ፣ዘሉክ ኢንቴሬርስ እና የፍቅር የተሰኙ ኢንተርፕራይዞች መሆናቸውንም ሰምተናል፡፡

በአባቱ መረቀ
ሰኔ 4 ቀን 2012 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.