ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ በተደረገው 6630 የላብራቶሪ ምርመራ አንድ መቶ ስልሳ አራት (164) ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ተገኝቶባቸዋል፡፡
በአጠቃላይ በሀገራችን ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር ሁለት ሺህ ስድስት መቶ ሰባ (2670) ደርሷል፡፡
በሌላ መልኩ በትላንትናው ዕለት ሰላሳ ሶስት (33) ሰዎች (32 ከአዲስ አበባ እና 1 ከአማራ ክልል) ከበሽታው ያገገሙ ሲሆን ይህም በአጠቃላይ በኢትዮጵያ ከበሽታው ያገገሙ ሰዎች ቁጥር አራት መቶ ሰላሳ አራት (434) ደርሷል።
እንዲሁም በቫይረሱ ተይዘው የነበሩ አምስት (5) ኢትዮጵያዊያን ህይወት ያለፈ ሲሆን ይህም ህይወታቸው ያለፈ ሰዎችን ቁጥር አርባ (40) አድርሶታል፡፡
ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን፣ዜናዎችን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ።
ሰኔ 4 ቀን 2012 ዓ.ም











