ምርጫው መተላለፉ ካልቀረ የህዝብና ቤት ቆጠራ በመሀከሉ ማካሄድ አስፋላጊ ነው ይላሉ የኦፌኮው አባል አቶ ጃዋር መሀመድ፡፡
ይህንን ማድረግ ደግሞ የምርጫውን ቅቡልነት ፤የምርጫውን እና የመንግስትን ተአማኒነት ከፍ ያደርገዋል ፡፡
መንግስትም ይህንን እንደሚያደርግም አምናለሁ ይላሉ አቶ ጃዋር፡፡
የህዝብና ቤት ቆጠራ ማድረግ አስፈላጊነት የጎላ መሆኑን ያነሱት አቶ ጃዋር ቀደም ባለው ጊዜ እንደ ሱማሊ ክልል እና የአማራ ክልል ሲያነሱት የነበረው ጥያቄ በአግባቡ ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ አሳማኝ በሆነ መንገድ መሬት ለማስያዝ ማካሄዱ አስፈላጊ ነው ብለዋል፡፡
ቆጠራውን ከማካሄዳችን በፊትም ደግሞ የህዝብና ቤቶች ቁጠራው የሚካሄድበት ሂደት ቴክኖሎጂው አሳማኝ በሆነ መልኩ የፖለቲካው ድርጅቶች ፤የሀገሪቱ ልሂቃን መሪዎች ባሉበት ውይይት እና መተማመን መፍጠር ያስፈልጋል ባይ ናቸው፡፡
የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ አብን ምክትል ሊቀመንበር እና የስትራቲጂ ጥናት ሀላፊ አቶ ዮሱፍ ኢብራሂም በበኩላቸው የህዝብና ቤቶች ቆጠራ ሳይታወቅ የምርጫ ጣቢያዎችን መደልደል የሚቻል እንዳልሆነ አንስተው በዚያ ላይ በርካታ ያለፉ ችግሮች አሉ ብለዋል፡፡
በዚህ ሀገር ላይ ፍትህ አልሰፈነም፤ በሰብአዊ ጥሰት ሲከሰስ የነበረው መንግስት አሁን ሰብአዊ መብት ሲጣስ ዝም ብሉ ተመልካች ሆኗል፡፡ይህ መጀመሪያ ሊታረም ይገባል ይላሉ አቶ ዮሱፍ፡፡
በዚያ ላይ በበርካታ ሀገራዊ ጉዳዩች ላይ መግባባት አልተደረሰም የሚሉት ምክትል ሊቀመንበሩ በዘረኛው አገዛዝ የተወሰኑ ህዝቦች ተገለው ፤ተገፍተው የሀገር አካል እንዳይሆኑ ተደርጓል፡፡
ስለሆነም የህዝብና ቤቶች ቆጠራ ቀድሞ መደረግ አለበት ከዚያ ምርጫው ማካሂድ ይቻላል ብለዋል፡፡
በያይኔ አበባ ሻምበል
ሰኔ 4 ቀን 2012 ዓ.ም











