አሜሪካ በአለም አቀፉ የጦር ወንጀሎች ፍርድ ቤት ላይ ማዕቀብ ጣለች።

የአሜሪካን ፕሬዚደንት ዶናልድ ትራምፕ በአለም አቀፉ የጦር ወንጀሎች ፍርድ ቤት ላይ ማዕቀብ እንዲጣል ፍቃድ መስጠታቸው ተነግሯል ።

አልም አቀፉ የጦር ወንጀሎች ፍርድ ቤት ላይ ማዕቀብ እንዲጣል ፕሬዝዳንቱ ፍቃድ መስጠታቸው ዋና ምክንያት የአሜሪካን ህዝብ ጥቅም የሚጉዳ እና የሀገራችንን ሉዓላዊነት የሚጥስ ምርመራ ለማድረግ ፍርድ ቤቱ በማቀዱ ነው ተብሏል ።

አልጄዚራ እንደዘገበው ፣ አሜሪካ የጦር ወንጀል መፈጸሟን ለማረጋገጥ በቀጥታ ምርመራ ላይ የተሰማሩ የአለም አቀፉ የጦር ወንጀሎች ፍርድ ቤት ሰራተኞች ላይ የጉዞ እገዳ መጣሏም ተነግሯል ።

ከዚህ በተጨማሪ ምርምራ የሚካሄዱ ሰራተኞች በቤተሰቦቻቸው ላይም የጉዞ እገዳው ተግባራዊ ይደረጋል ተብሏል ።

አለም አቀፉ የጦር ወንጀሎች ፍርድ ቤትም አሜሪካ ላይ ምርመራ እንዲጀምር ትዕዛዝ መስጠቱ ተነግሯል ።

ፍርድ ቤቱ አሜሪካ በአፍጋኒስታን የጦር ወንጀል መፈጸሟን ለማረጋገጥ በወታደሮቿ እና በደህነንት ባለስልጣናት ላይ ምርመራ ለማድረግ ውሳኔውን ማሳለፍ ተገልጿል ።

አለም አቀፉ የጦር ወንጀሎች ፍርድ ቤት ላይ ምርመራ እንዲጀምር የሩሲያ ግፊት እንዳለበት የአሜሪካን ባለሥልጣናት መናገራቸው ተገልጿል ።

ባለስልጣቱ ሩሲያ በፍርድ ቤቱ ውሳኔ ላይ እጇ አለ ቢልም ምንም አይነት ዝርዝር መረጃ ማቅረብ አልቻሉም ተብሏል ።

አሜሪካ በተደጋጋሚ የአለም አቀፉ የጦር ወንጀሎች ፍርድ ቤት ውሳኔዎች ውድቅ ማድረጓ ተዘግቧል ።

ፍርድ ቤቱ በአሜሪካ ህዝብና በአጋሮቿ ላይ ሀላፊነት የጎደለው እና ተጠያቂነት የሌለው ስራ እየሰራ መሆኑ የነጩ ቤተ መንግስት ባለስልጣናት ተናግረዋል ።

የትራምፕ መንግስት ከፓሪሱ የአየር ንብረት ለውጥ ስምምነት መውጣት ጀምሮ በሌሎች ተመሳሳይ አለም አቀፍ ድርጅቶችን መውጣት እንደቀጠሉ ነው በቅርብም ከአለም ጤና ድርጅት ጋር ቅራኔ ውስጥ መግባታቸው ይታወሳል።

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን፣ዜናዎችን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ። https://t.me/ethiofm107dot8

በዳንኤል መላኩ
ሰኔ 5 ቀን 2012 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.