የአሜሪካ ጦር መሪ ማርክ ሜሊ ፕሬዚደንት ዶናልድ ትራምፕን በመሸኘታቸው አሜሪካውያንን ይቅርታ ጠየቁ።

የአሜሪካ ከፍተኛ የጦር ጀነራል ማርክ ሜሊ ፣ ፕሬዝዳንት ትራንፕን ነጩ ቤተ መንግስት አካባቢ በነበረ ሰላማዊ ተቃውሞ ወታደራዊ እጀባ በማድረጋቸው እንደተጸጸቱ ተናግረዋል ።

ሲ ኤን ኤን እንደዘገበው ፣ ጀነራሉ የጆርጅ ፍሎይድ ግድያ ፣ በክፍለ ዘመኑ በአፍሪካን አሜሪካን ላይ የተፈጸመ ኢ ፍትህዊ ድርጊት ነው ብለዋል ።

በዚህ ፍትህ መጓደል በተቀሰቀሰው ሰላማዊ ተቃዉሞ በርካታ ዜጎች ያለምን ጥፋት ሰላማዊ ተቃውሞ ማካሄዳቸው የሚኮራ መሆኑን ጀነራል ማርክ ተናግረዋል ።

በአሜሪካን ጦር ውስጥ በከፈተኛ የስልጣን እርክን ላይ ያሉ አፍሪካን አሜሪካን 7 በመቶ ብቻ ነው ቀጣይ ይህም መስተካከል አለበት ብለዋል ጀነራሉ።

የፌደራል ጦሩም በአሜሪካን ጎዳናዎች ላይ እዲሰፍር መደረጉ ተገቢ አደለም ፣ እኔም ፕሬዚደንቱን ወደ ቤተ መቅደስ ሲጓዙ መሸኝቴ ተገቢ አይደለም ብለዋል ።
ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን፣ዜናዎችን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ። https://t.me/ethiofm107dot8

በዳንኤል መላኩ
ሰኔ 5 ቀን 2012 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *