የጀርመኑ ሉፍታንዛ አየር መንገድ 22 ሺህ ሠራተኞችን ሊቀንስ መሆኑን አስታወቀ።

አየር መንገዱ በኮርና ቫይረስ ባጋጠመው ኪሳራ ምክንያት 22 ሺህ የሚሆኑ ሠራተኞችን ለመቀነስ ማሰቡ ተሰምቷል፡፡

የኮሮና ቫይረስ በአቬሽን ኢንዱስትሪ ላይ ከፍተኛ ኪሳራ እያደረሰ እንደሚገኝ የሚታወቅ ሲሆን ከወረርሽኙ ማግስት የሉፍታንዛ አየር መንገድ አንድ መቶ አውሮኘላኖችን ሊያጣ እንደሚችል ዘገባው አስታውቋል፡፡

ግማሽ የሚሆነው የሠራተኞች ቅነሳ በጀርመን እንደሇነ የገለፀው አየር መንገዱ ለዚህም ከአጋር ድርጅቶች እና ህብረት ሥራ ማህበራት ጋር ስምምነት ላይ ደርሻለሁ ብሏል፡፡

የሉፍታንዛ አየር መንገድ 135 ሺህ ሠራተኞች ያሉት ሲሆን ግማሽ የሚሆኑት ደግሞ በጀርመን የሚገኙ ናቸው፡፡

የአየር መንገዱ የሠራተኞች ዳይሬክተር ሚሼል ኒግማን የአብዛኞቹን ሠራተኞች የሥራ ቅጥር ሳናቋርጥ ሥራውን ለማስቀጠል እንሠራለን ማለታቸውን ብሉምበርግ ዘግቧል፡፡

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን፣ዜናዎችን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ። https://t.me/ethiofm107dot8

በአባቱ መረቀ
ሰኔ 5 ቀን 2012 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *