በአዲስ አበባ ባለፉት ሁለት ቀናት በተከሰቱ ሁለት አደጋዎች ከ180 ሺ ብር በላይ የሚገመት ንብረት መውደሙ ተገለጸ።

በአዲስ አበባ እሳት አደጋ ስራ አመራር ኮሚሽን የህዝብ ግንኙነት ቡድን መሪ አቶ ጉልላት ጌታነህ ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንዳሉት የመጀመሪያው አደጋ በአቃቂ ክፍለ ከተማ ወረዳ 1 በቀን 6 2012 ዓ.ም ከ ቀኑ 8 ሰዓት የተከሰተ፤ 250 ካሬ ሜትር የሚሸፍን ድንገተኛ የሼድ ቃጠሎ ነው፡፡

በአደጋውም 30 ሺ ብር የሚገመት ንብረት የወደመ ሲሆን 500 ሺ ብር የሚገመት ንብረት ማትረፍ ተችሏል፡፡

ሌላኛው አደጋ የተከተው በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ወረዳ 6 ትናንት ምሽት ላይ 5 ሰዓት በሲሊንደር ጋዝ ማምረቻ ፋብሪካ ላይ የደረሰ ቃጠሎ ነው፡፡

ወደ 200 ካሬ ሜትር የሸፈነው የሲሊንደር ጋዝ ማምረቻ ፋብሪካ ቃጠሎው 150 ሺህ ብር የሚጠጋ ንብረት እንዲወድም ምክንያት የሆነ ሲሆን 15 ሚሊየን ብር የሚገመት ንብረት ደግሞ ማትረፍ መቻሉን አቶ ጉልላት ለጣቢያችን ተናረዋል፡፡

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን፣ዜናዎችን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ። https://t.me/ethiofm107dot8

በትግስት ዘላለም
ሰኔ 8 ቀን 2012 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.