በአውስትራሊያ አንድ ግለሰብ በህልሙ ያለመውን የገንዘብ መጠን በእውን ዓለም ማሸነፉ አግራሞትን ፈጥሯል።

ዜግነቱ አውስትራሊያዊ የሆነው ግለሰብ በህልሙ የተመለከተውን የሎተሪ እጣ ማሸነፉ ነው የተነገረው፡፡

ግለሰቡ ከዚህ በፊት ሎተሪ ቆርጦ የነበረ ሲሆን በህልሙ አሸናፊ የሚያደርገው የሎተሪ እጣ እንደወጣለት በህልሙ ያያል።

ከእንቅልፉ ሲነቃ ነገሩ ህልም በመሆኑ ብስጭት ገጥሞት እንደነበረ ይሄው ግለሰብ ተናግሯል።

ብስጭቱን ለባለቤቱ የተናገረው ይህ ግለሰብ በባለቤቱ ምክር መሰረት ህልሙ እውነት ሊሆን ይችላልና ወደ ሎተሪ አወራራጅ ድርጅት ደውሎ አሸናፊ ቁጥሩን እንዲያመሳክር ምክረ ሃሳብ ይቀርብለታል።

ይሄን ሲያደርግ ግን ግለሰቡ የ830 ሺህ ዶላር ሎተሪ እጣ አሸናፊ መሆኑ ይነገረዋል።

ግለሰቡ በደረሰው ገንዘብ እደሜ ልኩን ሲያልማቸው የነበሩትን ምኞቶች ለማሳካት እንሚያውለውም መናገሩን ዩፒአይ ዘግቧል።

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን፣ዜናዎችን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ። https://t.me/ethiofm107dot8

በሔኖክ ወ/ገብርኤል
ሰኔ 9 ቀን 2012 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.