አሜሪካ የፀረ-ወባ መድሀኒትን ለድንገተኛ ጊዜ ከምትጠቀማቸው መደሀኒቶች ዝረዝር ውስጥ አስወጣች፡፡

አሜሪካ ለድንገተኛ ጊዜ ለኮሮና ቫይረስ ተጠቂዎች ትሰጠው የነበረውን የፀረ-ወባ መድሀኒት ሀይድሮክሲ-ክሎሮኪዩን መጠቀም ማቆሟን የሀገሪቱ የምግብ እና መድሀኒት ቁጥጥር ባለስልጣን አስታውቋል፡፡

ባለስልጣኑ በአውሮፓውያኑ መጋቢት ወር ላይ በኮሮና ቫይረስ ታማዎች ላይ ለሚከሰቱ አንዳንድ ከባድ የጤና ጉዳዮች መድኃኒቱ ጥቅም ላይ እንዲውል ፈቅዶ ነበር፡፡ አሁን የፀረ ወባ መድሀኒት ለኮሮና ቫይረስ ህክምና መፍትሄ ይኖረዋል ብሎ ማሰብ ዘበት መሆኑን ከተካሄደው አዲስ ክሊኒካል ሙከራ ማረጋገጥ ችያለሁ ብሏል፡፡

እንደውም ፀረ ወባ መድሀኒት ገዳይ የሆነውን ቫይረስ ለማከም ውጤታማ አለመሆኑን ባለስልጣኑ አስረግጦ ተናግሯል፡፡የወባ መድሀኒት ለኮሮና ቫይረስ ህክምና መዋል እንዳለበት ይፋ ያደረጉት የሀገሪቱ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ መድሀኒቱን ለ2 ሳምንታት ወስጄዋለሁ ምንም አይነት የጎንዮሽ ጉዳት አላስከተለብኝምና መድሀኒቱ ላይ ቅሬታ አይኖረኝም፤ እንደውም አንዳንድ ሰዎች መድሀኒቱ ህይወታቸውን እንደታደገላቸው ነግረውኛል ሲሉ መከራከራቸውን ቀጥለዋል ሲል ቢቢሲ ዘግቧል፡፡

የዓለም ጤና ድርጅትን ጨምሮ በዘርፉ ምርምር እና ሙከራ ያደረጉ ባለሙያዎች የፀረ ወባ መድሀኒት ለኮሮና ቫይረስ ህክምና ከዋለ በታማሚዉ ላይ እስከ ሞት የሚደርሱ ጉዳቶችን ሊያስከትል ስለሚችል መድሀኒቶቹን ከመጠቀም አንዲቆጠቡ ማስጠንቀቃቸውን ቀጥለዋል፡

፡ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን፣ዜናዎችን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ።

https://t.me/ethiofm107dot8

በትግስት ዘላለምሰኔ

9 ቀን 2012 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.