እንግሊዝ የኮሮና ተጠቂዎችን ከሞት የሚታደግ መድሃኒት ማግኘቷን አስታወቀች፡፡

የሃገሪቱ የጤናዉ ዘርፍ ተመራማሪዎች እንዳሉት፣ህክምናዉ ብዙ ወጭን የማይጠይቅ በመሆኑ ብዙሃኑን የህብረተሰብ ክፍል ተደራሽ ለማድረግ የሚያስችል ነዉ ብለዋል፡፡

መድሃኒቱ የሰዎችን የበሽታ መከላከል አቅም በማሳደግ ቫይረሱን በቀላሉ እንዲቋቋሙ የሚያደርግ መሆኑ ተነግሯል፡፡

በ2 ሺህ ታማሚዎች ላይ በተደረገ ጥናት የሟቾችን ቁጥር እስከ 40 በመቶ እንዲቀንስ አድርጓል ተብሏል።

ይህ መድሃኒትን ሰዎች በህክምና እንደሚታዘዝላቸው የመድሃኒት መጠን መሰረት ከ4 እስከ 35 ፓውንድ ወጪ ሊያወጡ ይችላሉም ተብሏል።

መድሃኒቱ ቀደም ብሎ መገኘት ቢችል በሃገሪቱ በቫይረሱ ምክንያት ከሞቱ ሰዎች ዉስጥ ቢያንስ 5 ሽህ ያህሉን ማትረፍ ይቻል እንደነበር ተመራማሪዎቹ ተናግረዋል፡፡

የመድሃኒቱ ወጭ ዝቅተኛ በመሆኑም በተለይም ለድሃ ሀገራትም ጭምር በቀላሉ ተደራሽ ማድረግ ይቻላል ነዉ የተባለዉ፡፡

ዴክሳ ሜታሶን የተሰኘዉ ይህ መድሃኒት የተገኘዉ በአለማቀፋ የመድሃኒት ጥናት አማካኝነት ሲሆን ለፈዋሽነቱ ማረጋገጫ እንደተሰጠዉ ቢቢሲ ዘግቧል፡፡

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን፣ዜናዎችን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ። https://t.me/ethiofm107dot8

በሙሉቀን አሰፋ
ሰኔ 9 ቀን 2012 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *