በአዜማን ሆቴል በለይቶ ማቆያ በነበሩበት ጊዜ 1 ሺህ ዶላር መሰረቃቸውን አንድ የሆቴሉ ደንበኛ ተናገሩ።

ግለሰቡ እንዳሉት ከውጭ አገር ወደ አገሬ በምገባበት ጊዜ መንግስት የኮሮና ቫይረስን ለመከላከል በሚል ያስቀመጠውን ትዕዛዝ በማክበር አዲስ አበባ ቦሌ ወደ ሚገኘው አዜማን ሆቴል በለይቶ ማቆያ መክረማቸውን ይናገራሉ።

በሆቴሉ ከቆዩ በኋላም ቫይረሱ እንዳለባቸው በምርመራ ከተረጋገጠ በኋላ ወደ ለይቶ ማከሚያ ተወስጄ ከቫይረሱ አገግሜ ስመለስ ግን በሆቴሉ ያስቀመጥኩትን ገንዘቤ ማግኘት አልቻልኩም ብለዋል።

አሁን ላይ ከኮሮና ቫይረስ ነጻ ተብለው ወደ ቤተሰቦቻቸው የተቀላቀሉት እኝህ ግለሰብ በሆቴሉ በቆየሁበት ጊዜ 1 ሺህ 60 ዶላር ተሰርቄያለሁ ብለዋል።

የአዝማን ሆቴል ባለቤት አየለ ገብርመድህን በበኩላቸው ፣ ክሱ የሆቴሉን ስም ለማጥፋት የተደረገ ጥረት ነው ፣ ቅሬታ አቅራቢው በተከራዩት ክፍል ውስጥ በሚገኝ ካዝና ገንዘቡን ማስቀመጥ ይችሉ ነበር ብለዋል፡፡

ግለሰቡ በሆቴላችን በቆዩበት ጊዜ ገንዘብ አልተሰረቁም ስም እያጠፉ ነው ሲል ምላሽ ሰጥቷል።

ገንዘቡን ይዘው ወደ ሆቴላችን ለመግባታቸው ማስረጃ የላቸውም ብሏል አዜማን ሆቴል።

በአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን የካራማራ ፖሊስ ጣቢያ የንብረት ነክ ቡድን ኃላፊ ምክትል ኢንስፔክተር መንግስቱ ገብረሚካሄል እንዳሉት ግለሰቡ በአዜማን ሆቴል በለይቶ ማቆያ በነበሩበት ጊዜ 1 ሺህ 60 ዶላር ተሰረቅሁ ሆቴሉም ሊተባበረኝ አልቻለም የሚል ክስ እንደደረሳቸው ገልጸዋል።

ይሁንና ፖሊስ በጉዳዩ ዙሪያ ምርመራ ጀምሬያለሁ ምርመራው ሲጠናቀቅ ይፋ አደርጋለሁ ብሏል።

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን፣ዜናዎችን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ። https://t.me/ethiofm107dot8

በዳንኤል መላኩ
ሰኔ 10 ቀን 2012 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.