የአሜሪካ፣ ብራዚል እና ፊሊፒንስ ፖለቲከኞች ሐሰተኛ የኮቪድ 19 መረጃን በማሰራጨት የሚስተካከላቸው የለም ተብሏል።

የሮይተርስ የዲጅታል ዜና ዘገባ የጥናት ተቋም አደረኩት ባለዉ ጥናት፣በተለያዩ ሀገራት የሚገኙና 80 ሽህ በሚሆኑ ሰዎች ላይ በተሰራ ጥናት፣ጥናቱ ከተደረገባቸዉ ሰዎች 40 በመቶ የሚሆኑት ለፖለቲከኞች ትኩረት እንደሚሰጡ ገልጾ የኮቪድ19ኝን በሚመለከት የደረሳቸዉ መረጃ ገና ከጅምሩ በስህተት የተሞላ መሆኑን ነግረዉኛል ብሏል፡፡

በተለይም በብራዚል፣ፊሊፒንስና አሜሪካ ፖለቲከኞች የኮቪድ 19ኝን በተመለከተ በተደጋጋሚ የተሳሳቱ መረጃዎችን በማሰራጨት ተወዳደሪ የላቸዉም ብሏል፡፡

በግሪክ፣ ደቡብ ኮሪያና አሜሪካ ደግሞ የመገናኛ ብዙሃን ባለሙያዎች ጭምር ፖለቲከኞቹ የሚሉትን በመከተል አሳሳች መረጃዎችን ሲያሰራጩ መቆያታቸዉን ጥናቱ ጠቁሟል፡፡

በጥናቱ መሰረት የጃፓንና የታይዋን መሪዎች መረጃን ላለማሳሳት የተሻለ ጥንቃቄ ያደረጉና ጥንቃቄያቸዉ የተሳሳተ መረጃ ከመስጠት የታደጋቸዉ መሆኑን ቢቢሲ ዘገቧል፡፡

የኮረና ቫይረስ በተከሰተበትና መነጋገሪያ በነበረበት ወቅት ዶናልድ ትራምፕ አንዴ የቻይና ቫይረስ፣በሌላ ጊዜ ደግሞ አሜሪካ የመከላከል አቅሙ ስላላት ስጋት አይግባቸሁ ሲሉ፤የብራዚሉ ቦልሶናሮም ብራዚላዊያን ከእንቅስቃሴ እንዳይታቀቡ ሲመክሩ እንደነበር አይዘነጋም፡፡

በአሁኑ ወቅት አሜሪካ 2 ነጥብ 16 ሚሊዮን ተጠቂዎችና 118 ሽህ ሞት በማስመዝገብ ከዓለም ቀዳሚ ስትሆን፣ ብራዚል ደግሞ ከ892 ሽህ በላይ ተጠቂዎችና ከ44 ሽህ በላይ ሞት በማስመዝገብ በሁለተኛነት ትከተላለች፡፡

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን፣ዜናዎችን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ። https://t.me/ethiofm107dot8

በሙሉቀን አሰፋ
ሰኔ 10 ቀን 2012 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *