ባለፉት አምሰት ቀናት ውስጥ ብቻ ከ16 ሚሊየን ብር በላይ ግምታዊ ዋጋ የወጣላቸው የኮንትሮባንድ ዕቃዎችና ንግድ ማጭበርበር ተያዙ።


ባለፉት ተከታታይ 5 ቀናት ውስጥ (ከሰኔ 6-10/12 ዓ.ም) ብቻ ግምታዊ ዋጋቸው ከ16 ነጥብ 3 ሚሊየን ብር በላይ የሚሆን የኮንትሮባንድ ዕቃዎችና ንግድ ማጭበርበር በቁጥጥር ስር ውሏል፡፡
በሁሉም የሀገርቱ መቆጣጠሪያ ጣቢያዎችና ኬላዎች ላይ በተለያዩ ስልቶችን በመጠቀም የኮንትሮባንድና የንግድ ማጭበርበር እንቅስቃሴዎችን የመቆጣጠር እና የማጋለጥ ስራ ተጠናክሮ ቀጥለዋል።


ከተያዙት የኮንትሮባንድ ዕቃዎች መካከል የተለያዩ ዓይነት አዳዲስና አሮጌ አልባሳት፣ የአዋቂና የህፃናት ጫማዎች፣ ኤሌክትሮኒክስ፣ ተሽከርካሪዎች፣ የተሸከርካሪ ጎማና መለዋወጫ የምግብ ዘይት፣ ጫት፣ ሃሺሽ እና ልዩ ልዩ ዓይነት የኮንትሮባንድ ዕቃዎች እንዲሁም በቦሌ፣ በሞጆ እና በአንዳንድ የጉምሩክ መቆጣጠሪያ ጣቢያዎች ላይ በተደረገው ከፍተኛ ቁጥጥር ብዛት ያላቸው የንግድ ማጭበርበር እንቅስቃሴዎች ተለይተው በቁጥጥር ስር እንዲውሉ የተደረገ ሲሆን 120,000 ሀሰተኛ ዶላርም በሞያሌ ቅርንጫፍ ተይዟል።


ስራው በጣም አድካሚ ቢሆንም ደከመኝ ሰለቸኝ ሳይሉ ቀንና ሌሊት ህዝባቸውንና ሀገራቸውን በብዙ መስዋዕትነት ውስጥ ሆነው እያገለገሉ ያሉ የጉምሩክ ኮሚሽን አመራሮች፣ ሠራተኞች እና የፀረ-ኮንትሮባንድ አካላት እንዲሁም ከሌሎች ተባባሪ አካላት ጋር በመሆን፣ በዚህ አስቸጋሪ ወቅት በየመቆጣጠሪያ ጣቢያዎች ላይ ኮንትሮባንዲስቶችን በማጋለጥና ህገ-ወጥ ዕቃዎችን በመቆጣጠር ውጤታማ ስራ እየተሰራ ይገኛል።

የጉምሩክ አመራሮችና ሠራተኞች ሙያው የሚጠይቀውን ስነ-ምግባር በማክበር በየደረጃው ካሉ የፀጥታ አካላት ጋር በመሆን የኮንትሮባንድ ዕቃዎችንና የንግድ ማጭበርበር እንቅስቃሴዎችን እንዲሁም ኮንትሮባንዲስቶቹን በሚያስተምር ሁኔታ እርምጃ በመውሰድ የተያዙ ዕቃዎች ለመንግስትና ለህዝብ ገቢ እንዲሆኑ መደረጉን ሚኒስቴሩ አስታውቋል።


ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን፣ዜናዎችን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ። https://t.me/ethiofm107dot8


የዩቲዩብ ገጻችንን ሰብስክራይብ በማድረግ ቪድዮቻችንን ይመልከቱ::

https://www.youtube.com/channel/UCn4D20GPsAtNqN5bIC1BhFA?sub_confirmation=1

ኢትዮ ኤፍ ኤም የኢትዮጵያዊያን

ሰኔ 11 ቀን 2012 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.