ለአስዋን ግድብ ውሀ የሚያቀርብ ግድብ ኢትዮጵያ ውስጥ ሊሰራ ታቅዶ እንደነበር ያውቁ ኖሯል?

እንግሊዝ ግብፅ ውስጥ በስፋት ጥጥ ታመርት ነበር፤ ያ ጥጥ ወደ እንግሊዝ ሄዶ የሱፍ ጨርቅ ይመረትበት ስለነበር፤ የአባይ ውሀ ፍሰት እንዳይቀንስ ትሰጋ ነበር፡፡

በአሜሪካን ሀገር መኖርያቸውን ያደረጉት የምህንድስና ባለሙያው እና በህዳሴው ግድብ ዙሪያ ጥናቶችን ለዓለም አቀፉ ማህበረሰብ በማሳወቅ የሚታወቁት አቶ ሲሳይ አለማየሁ ከኢትዮ ኤፍ ኤም ጋር ባደረጉት ቆይታ የግብጽ ፍላጎት ኢትዮጵያ መቼም ቢሆን በድህነት ውስጥ ስትዳክር አባይን ሙሉ ለሙሉ መቆጣጠር ነው ብለዋል።

እንግሊዞች በግብጽ እና በሱዳን ለከፈቷቸው ኢንዱሰትሪዎች ቋሚ የጥጥ አቅርቦት እንዲኖር ለማድረግም ቋሚ የውሀ አቅርቦት ያስፈልግ ነበር፡፡

አስዋን ግድብ እንደተገነባ፤ እድሜው እንዲረዝምና በቋሚነት ውሀ እንዲያቀርብ እንግሊዞች ኢትዮጵያ ውስጥ ግድብ እንዲገነባ አቋም ይዘው ነበር፡፡

የእንግሊዝ የመሀንዲስ ቡድንም ከሀይድሮሎጂስቶች ጋር በመሆን ጥናት አካሄዶ ነበር፡፡

አንደኛ እንደ ድርቅ ያለ የችግር ጊዜ ሲመጣ መጠባበቂያ ግድብ ውሀ እንዲለቅ ነበር የታሰበው፡፡

ሀይለኛ ጎርፍ ቢመጣም፣ እየበረደ ሱዳንን አልፎ ወደ ግብፅ ይደርሳል ተብሎ ታስቦ እንደነበር ነግረውናል፡፡

ሌላው እንግሊዞች በወቅቱ አስበውት የነበረው፤ በትነት ውሀ እንዳያጡ ይሰጉ ስለነበር፤ ከጣና ሀይቅ በመጥለፍ በቱቦ አድርጎ ውሀውን መውሰድ ነበር፡፡

አሁን ግብፅ ከኢትዮጵያውያን መቀነት ተፈቶ በመዋጮ የተሰራውን ታላቁን የህዳሴ ግድብ ፤ ያንን የቅኝ ግዛት ጊዜ ህልም ማስፈፀሚያ ልታደርገው ነው የምታስበው እያሉ ነው የመስኩ ባለሙያዎች።

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን፣ዜናዎችን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ። https://t.me/ethiofm107dot8

በሔኖክ አስራት
ሰኔ 12 ቀን 2012 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.